PSTS

“ለሌሎች ተቋማት ሞዴል መሆን የሚችል ድርጅት ነው፡፡”

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማት ፣ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ።ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አስከአሁን ያለውን የሥራ ሂደት፣ ያጋጠሙ ፈተናዎችና የተገኙ ውጤቶችንና ስኬቶችን እንዲሁም ድርጅቱ በቀጣይ ለ10 ዓመታት የሚመራበትን ዕቅድ ለመገምገም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማት ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ግንቦት 28 ቀን ጠዋት ቢሾፍቱ ያቱ ሆቴል ተገኝተዋል፡፡የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ ለተከበሩ የምክር ቤት አባላት “የእንኳን ደህና መጣችሁ“ ንግግር ካደረጉ በኋላ ድርጅቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ የቋሚ ኮሚቴው አባላት የድርጅቱን እንቅስቃሴ በመገምገም ጠንካራ ጎኖቻችን እንዲጠነክሩና መስተካከል ያለባቸውን ጉድለቶች በመጠቆም ባሳዩት ያሳለሰ ጥረት ድርጅቱ የላቀ የጥራት የምስክር ወረቀት ተሸላሚ እንዲሆን ያበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር ጠቁመው የቋሚ ኮሚቴው አባላትን በድርጅቱና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሯ ድርጅቱ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ከመስከረም 5 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ያለፈባቸውን ውጣ ውረዶችና ስኬቶች ያቀረቡ ሲሆን የ10 ዓመቱ የድርጅቱ መሪ እቅድም ለቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ቀርቦ ዝርዝር ውይይት ተደርጎበታል፡፡ “የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አገልግሎት መስጠት የጀመረበት ጊዜ አጭር ይሁን እንጂ በተለያዩ ጊዜያት በሚያካሂደው የለውጥ ስራ በሀገራችን ስኬታማ ከሆኑ ድርጅቶች መካከል ተጠቃሽ እንዲሆን አስችሎታል፣ ለሌሎች ተቋማት ሞዴልና አርአያ ሊሆን የሚችል ድርጅት ነው“ያሉት የቋሚ ኮሚቴው አባላት በአለም አቀፍ መስፈርቶች ተወዳድሮ ልዩ የአድናቆት ጥራት ተሸላሚ በመሆኑ መደሰታቸውንና ገልጸው “ ከዚህ ድርጅት ጋር መስራታቸው እጅግ እንዳኮራቸው “ተናግረዋል፡፡ “በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን ያከናወነ ድርጅት ከመሆኑ ባሻገር በተለይ የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛው ጠዋት በጊዜ ከስራ ገበታው ላይ ተገኝቶ ማታም ወደ ቤቱም በጊዜ እንዲገባ በማስቻል ሰራተኛው ለሀገሩ ሙያዊ አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ድርጅቱ ያበረከተው አስተዋጽኦ በጥቂት ቃላት ብቻ የሚገለፅ አይደለም፡፡” ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አሸናፊ ዳኤማ “እንደ ቋሚ ኮሚቴ በድርጅቱ አካሄድ ላይ ይህ ጎደለ የምንለው ነገር ባይኖርም ያሉትን ጠንካራ ጎኖች አዳብሮ ቀጣዩን 10 ዓመት በስኬት እንደሚወጣ ባለ ሙሉ ተስፋ ነን ፣ የድርጅት ሰኬትም ከሀገራችን አልፎ በአፍሪካ ደረጃ ተመራጭ ለመሆን ያቀደው ዕቅድ እንደሚሳካለት አንጠራጠርም››” ብለዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው አባላት “ በተግባር ባየነው የተሳካ እንቅስቃሴ እጅግ ተደስተናል፡፡ ለድርጅቱ ስኬት መሪ የሆኑት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወትን ትልቁን ፣የማኔጅመንት አባላቱንና መላውን ሰራተኛ ላገኛችሁት ስኬት እንኳን ደስ ያላችሁ በቀጣይ ጠንክራችሁ በመስራት የበለጠ ውጤት እንድታስመዘግቡ አደራ እንላለን፡፡” ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማት ፣ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ተናግረዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *