የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፓርት በአለም አቀፍ መስፈርት መሠረት በተደረገ ውድድር የከፍተኛ አድናቆት የጥራት የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል።የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በጥራት ሲታጀብ ለአገር እድገት ወሳኝ ነው – አቶ ታገሰ ጫፎመጋቢት 19 ቀን 2013 (ኢዜአ) የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በጥራት ሲታጀብ ለአጠቃላይ አገራዊ እድገት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ከኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመሆን የመንግስት አገልግሎት ጥራት ላይ ያዘጋጀው ልዩ ውድድር ማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሂዷል።በመርሃ ግብሩ ላይ 10 የፌዴራል መንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደታቸው ተመዝኖ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።ከአስሩ መካከል የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በተሻለ መልኩ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት በመቻሉ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ቲቢ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ደግሞ የከፍተኛ ማዕረግ ተሸላሚ ሆነዋል።የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን የማዕረግ ተሸላሚ ሆኗል።የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ደግሞ የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ሲወስድ አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ ተቋም የአፈፃፀም ውጤቱ ዝቅተኛ ነው ተብሏል።የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራቸኞች ትራንስፓርት አገልግሎት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት ትልቁ ለመላው ሰራተኛ፣ለማኔጅመንት አባላትና ለድርጅቱ ስራ አመራር ቦርድና ለድርጅቱ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በሙሉ ውጤቱ የጋራ ነዉና እንኳን ደስ ያላችሁ ቡለዋል።