PSTS

“በቀጣይ ዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን ዛሬን ከመቼውም ጊዜ በላይ አገልግሎታችን በጥራት መሰጠት ይኖርብናል ፡፡” ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ

ከ10ታላላቅ ተቋማት ጋር ተወዳድሮ የከፍተኛ አድናቆት የምስክር ወረቀት ያገኘው የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖት አገልግሎት ድርጅት በሚቀጥለው ዓመት ከዚህ በላቀ ትጋትና ክንውን የተሻለ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ለላቀ ውጤት መብቃት ይኖርበታል ሲሉ የድርጅቱ ሰራተኞች ገልጸዋል፡፡ “የተገኘው ውጤት የሰራተኛው ፣የማኔጅመንቱ የስራ አመራር ቦርዱና የአገልግሎታችን ተጠቃሚ በጋራ ለአንድ አላማ በመስራታችን ነው፡፡”ያሉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ “ካገኘነው የአድናቆት የምስክር ወረቀት በላይ አገልግሎት የምንሰጠውን ተገልጋይ በጥራት ማስተናገዳችን በመረጋገጡ የበለጠ ያስደስተናል፡፡”ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “ያገኘነው ሽልማት የሚያኩራራ ሳይሆን የበለጠ እንድንሰራ አደራ ጭምር በመሆኑ ሁላችንም በተሰማራንበት የሙያ መስክ ጠንክረን መስራት አለብን :: ጠንክረን ከሰራን ደግሞ በጥቂት ነጥቦች ያጣነውን ዋንጫ በቀጣይ የማናገኝበት ምክንያት የለም፡፡”ሲሉ ዋና ዳይሬክተሯ ለድርጅቱ ሰራኞች ገልፀዋል፡፡“ብዙ አቅም ቴክኖሎጂና የሰው ኃይል ካላቸው ድርጅቶች በጥራት ልቀን በመገኘት ባገኘነው ውጤት እጅግ ተደስተናል፡፡”ያሉት የድርጅቱ ሰራተኞች “በሽልማቱ ተበረታተን በተሰማራንበት የሙያ መስክ ሁሉ ጠንክረ ዲሲፕሊንና በጥራት ስራችንን በመስራት በቀጣይ አሁን ካገኘነው ሽልማት በላይ ለማግኘት እንደምንጥር ቃል እንገባለን፡፡”ሲሉ ገልጸዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *