ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ አስገንብቶ ስራ ያስጀመረው የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ በትክክል ተምረው መንጃ ፍቃድ ለማግኘት የሚፈልጉትን አሽከርካሪዎች ብቻ ተቀብሎ በማሰልጠን ላይ ሲገኝ በሚሰጠው ልዩ ልዩ የቴዎሪና የተግባር ስልጠና በሰልጣኞች ዘንድ አድናቆትን ያገኘ ተቋም ሆኗል፡፡
“የተሸከርካሪ አደጋ በበዛባት ሀገራችን ተባብረንና ተረባርበን አደጋውን መከላከል ካልቻልን ውጤቱ የከፋ ይሆናል፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙን የአደጋው መንስኤ አብዛኛው የአሽከርካሪው ችግር በመሆኑ አላማችን በትክክለኛ መንገድ ማሽከርከርን ተምሮና ህጉን አውቆ ማስረጃ የሚሰጠውን ዜጋ ለማፍራት ነው፡፡ ” የሚሉት የፐብሊክ ሰርቪሰ ትራንስፖርት አገልግሎት የአሸከርካሪዎች አሰልጣኝ አቶ ያሬድ “የማሽከርከርን ክህሎት ከትራፊክ ህግና ደንብ ጋር በማቀናጀት ከምንሰጠው ስልጠና ባሻገር የተሸከርካሪ አካላትንና ግብአትን አውቀው ብልሽት ሳያጋጥማቸው በፊት መፍትሔ የሚፈልጉ የቴክኒክ ዕውቀት ያላቸውን አሽከርካሪዎች በመፍጠር ላይ እንገኛለን፡፡” ይላሉ፡፡
“ብዙዎች የራሳቸውንና የወገናቸውን ህይወት በተሸከርካሪ አደጋ ያጡ ግለሰቦች የኋላኋላ ፀፀትን ለራሳቸውንና ለቤተሰቦቻቸው ጥለው የሚያልፉት በማወቅም ሆነ በቸልተኝኘት በሚፈጥሩት ችግር ነው፡፡ ወደ እኛ ለመሰልጠን የሚመጡ አብዛኞቹ ህግና ስርዓትን አውቀው ፣አንድ አሽከርካሪ ሊኖረው የሚገባውን ብቃት ቀስመው ፣በራስ መተማመናቸው ዳብሮ መንጃ ፍቃድ ለማውጣት የሚፈልጉ ናቸው ፡፡ ብቁ ሊያደርግ የሚችለውን የስለልጠና ጊዜ ያለምንም ማቆራረጥ ተምረው ሲጨርሱና ፈተናውን ሲያልፉ ብቻ ማስረጃው የሚሰጥ መሆኑን አምነው የሚመጡና ኃላፊነትን የሚሰማቸው ናቸው፡፡ የሚሉት አሰልጣኙ “ከብልሹ አሰራር የጸዳ ንፁሃንን የአደጋ ሰለባ የማያደርጉ አሽከርካሪዎችን ለሀገር ለማበርከት በምናደርገው ጥረት ያገኘነው ውጤት አበረታች ነው፡፡” ብለዋል፡፡
“በቅርቡ በከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ ወደ አልግሎታችን የገባውና አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው ምስለ ተሸከርካሪ (ሲሙሌተር) እጅግ ዘመናዊና በአሁኑ ሰዓት በአለም ላይ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ውጤት በመሆኑ ስራችንን የበለጠ የተቀላጠፈ ያደርገዋል፡፡ ከፈረንሳይ ሀገር በመጡ ባለሙያዎች በተሰጠው ስልጠና አማካኝነት በትክክለኛ ተሸከርካሪ ላይ የመሰልጠን ያህል ስሜት የሚፈጥረው ይኸው አዲስ ማሰልጠኛ ማሽን እንደአየሩ ሁኔታ የሚለዋወጥ ዳገት፣ ቁልቁለት፣ ሌሊት፣ ቀን ሁሉንም የሚመስል በመሆኑ ለሰልጣኞቹ ተስማሚ ነው፡፡” ብለዋል፡፡
“አዲሱ ሲሙሌተር ምስለ ተሸከርካሪ ሁሉንም የአነዳድ ሁኔታ ሪፖርት የሚያደርግና መዝግቦ የሚይዝ በመሆኑ ለችግር እንዳይጋለጥ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ያሬድ “አሁንም የማሽከርከርን ጥበብ በተገቢው ስፍራ፣ ማቴሪያልና ባለሙያ መሠልጠን የሚፈልጉ ዘሽከርካራች እንዲመጡ ጋብዘዋል፡፡
ቀልድ ነው። ማሰልጠኛ ያለ አቅማችሁ መክፈት አልነበረባችሁም።
እዚህ ለመማር የተመዘገበ ካለ ለመጉላላት ይዘጋጅ።