• ኢትዮጵያ ውስጥ ያጋጠመው ንረት፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች እየጎዳ መሆኑን በጽኑ እንገነዘባለን፤ ችግሩ ላለፉት 20 ዓመታት የማያቋርጥ የዋጋ ንረት በመፈጠሩ የመጣነው፡፡
• በተጨማሪም ሸማች እና አምራች መካከል ያለውን ክፍተት ማስተካከል አልተቻለም፤ ጦርነት፣ ድርቅ፣ የአጋር አካላት እርዳታ መቀነስ እና ወደ ከተማ ፍልሰት መጨመር ዋና ዋና ምክንያች ናቸው፡፡
• እየተተገበሩ የሚገኙ መፍትሄዎች፥ የምርት አቅርቦት ላይ በስፋት መስራት፣ የምገባ ማእከል እና የማዕድ ማጋራት ስርዓትን ማስፋት ናቸው፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ደጎማዎች እየተደረጉ ነው፣ ለምሳሌ ነዳጅ ባለፉት 8 ወራት 50 ቢሊየን ብር በላይ ተደጉሟል፡፡ 133 ሺህ ገደማ ተሸከርካሪዎች ድጎማ ያገኛሉ።