ለፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልገሎት ሰራተኞች የካይዘን ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎርፉ ጌታቸው እንዳሉት “ካይዘንን በአገልግሎታችን ውስጥ መተግበራችን ለስራችን መሳካትና አስተዋጽኦ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ በመሆኑም ስልጠናውን መውሰዱ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ የስራ ክፍል የወሰደውን ስልጠና በተግባር ማሳየት እንዳለበትና በተጨማሪም ስራው መሰራቱን ክትትል መደረግ እንዳለበት ለሰልጣኞች ገልጸዋል፡፡ሰልጣኞችም ስልጠናው በጣም ጥሩ መሆኑንና እንደተደሰቱበትም ገልፀው ቀጣይነትሊኖረው ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል፡፡
የስልጠናው ይዘትም ካይዘን
Ø ትርጉምና ጠቀሜታው
Ø 8ቱ የብክነት አይነቶችን በተመለከተ በሰፊው የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡