በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከበረ
በሀገራችን ለ47ተኛ ጊዜ ‘’ የእህቴ ጠባቂ ነኝ’’እንዲሁም በአለም አቀፍ ለ112ተኛ ጊዜ ‘’INNOVATION AND TECHNOLOGY FOR GENDER EQUALITY’’ በሚል መሪ ቃል በአገልግሎቱ አመራሮችና ሰራተኞች ተከብረዋል።
የአገልግሎቱ የስርዓተ ጾታና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ታደሰ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነት ለማረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ እና ’’ሴትን ማክበር የዘመናዊነት መገለጫ በመሆኑ የሴቶችን እኩልነት በተግባር ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል’’ የበአሉ ተሳታፊዎችም በጣም ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።