PSTS

“ከአውቶቡሱ ምቾት …. የሰራተኞቹ ታማኝኘት….. አላህ ይስጥልን”

ወጣት ኢክረም ድሌ

*********//*********

ኢክረም ድል ትባላለች ።የጅማ ነዋሪ ናት። ጉዳይ ይገጥማትና ከጅማ ወደ አዲስ አበባ በአዲሱ ጥራትና ብቃት ባለው የፐብሊክ ሰርቪስ ሀገር አቋራጭ አውቶቡስ ተሳፍራ ትመጣለች።

“ምቾት ያለው ዋይፋይና መፀዳጃ የተገጠመለት ፣ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ለመጓዝ ፍላጎቴ ስለሆነ መርጬ ነው የተሳፈርኩት፡፡” የምትለው ኢክረም በአውቶቡሱ ምቾት ፣በአሽከርካሪው እርጋታ ፣በጉዞ አስተናጋጇ ትህትና ታጅባ አዲስ አበባ ደረሰች፡፡

ኢክረም አዲስ አበባ ደርሳ በችኮላ ዕቃዋን ሸክፋ ወደ ቤቷ ተጓዘች ፡፡ ይሁን እንጂ “ድንገት የእጅ ስልኬ ስፈልግ አጣሁት። ቦርሳዬን ባገላብጥ ሻንጣዬን ብፈትሽ ላገኘው አልቻልኩም ፡፡ ሌባ ሰርቆኛል ብዬ አሰብኩ የኋላ ኋላ ግን አውቶቡስ ውስጥ እንደጣልኩት ተረዳሁ፡፡ የጨነቀኝ የሞባይሉ መጥፋት ሳይሆን በውስጡ ያለው መረጃና ፎቶ እጅግ ቆጨኝ ።ይሁን እንጂ ጅማ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ወኪል ነበርና ወደዚያው ደውዬ ስልክ እንደጠፋኝ ገለፅኩላቸው፡፡

“ይገኛል ብዬ ባላስብም ምናልባት ብዬ ያመለከትኩት ውጤታማ ሆነ ።አላህ የባረካት አስተናጋጅ ስልኩን አግኝታ መለሰችልኝ ፡፡ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡” ስትል ኢክረም ቢሮ መጥታ ተናግራለች፡፡

የጉዞ አስተናጋጅ ፀሐይ ኃይሉ “የሰው ገንዘብ የሰው ነው፡፡ ፐብሊክ ሰርቪስ ወደ ስራ ከመግባታችን በፊት ስለታማኝነትና ደንበኛ አያያዝ በተመለከተ በቂ ስልጠና ሰጥቶናል፡፡ ሞባይሉን እኔ ለጥቅሜ ባውለው የሚጠፋው የድርጅቴ ስም ነው፡፡ ታማኝ ሆኜ በመመለሴ ክብሩ የእኔ ብቻ ሳይሆን የተቋሙና የሰራተኛው ነው፡፡ ኢክረም አላህ ይስጥልኝ ብላ መርቃኛለች ።ከዚህ በላይ ደስታ የለም ብዙ መረጃ ያለውን ሞባይሏን ሳስረክባት ፊቷ ላይ ያየሁት ደስታ ለኔ ከደስታም በላይ ነበር፡፡” ብላለች

“ከአውቶቡሱ ምቾት ባልተናነሰ የሰራተኞቹ ታማኝነት ገዝቶኛል፡፡ የሁልጊዜም ደንበኛ ነኝ ።ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ድረስ መጥቼ ለማመስገን የፈለጉትም የተሰማኝ ከፍተኛ ደስታ ስለሆነ ነው፡፡ አላህ ይስጥልኝ አመሰግናለሁ፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *