የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንሰፖርት አገልግሎት የመስተንገዶ ሰራተኛ ያገኘችውን ስማርት ሳምሰንግ ሞባይል ለባለቤቱ መለሰች።
**********//**********
በአገልግሎቱ የአገር አቋራጭ መኪና የጎን ቁጥሩ 9021 ከሚዛን ወደ ጅማ በመጓዝ ላይ የነበሩት አቶ ውጅማ ታንቁ ስልካቸውን መኪናው ላይ ጥለው በመውረዳቸው የመስተንግዶ ሰራተኛ የሆነችው ወጣት ጤናዬ ተሻገር ስልኩን በማግኘቷ ለባለቤቱ መመለሷ ተገልፀዋል፡፡
የስልኩ ባለቤትም “ስልኬን አገኘዋለሁ ብዩ አላሰብኩም ነበር ታማኟ አስተናጋጅ ግን ስልኩ ሳያጓጓት ልትመልስልኝ ችላለች “ በማለት አመስገነው ተረክበዋል፡፡
“የአገልግሎቱ ባስ ካፒቴኖችም ሆኑ የመስተንግዶ ሰራተኞች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት በተግባቦት፣ በስነምግባር ና ፀረ ሙስና ስልጠና ተሰጥቷቸው ስለሚገቡ በታማኝነታቸውና በስነምግባራቸው የታነፁ ናቸው፡፡“ በማለት ተናገሩት የስነ ምግባር ሀላፊው አቶ ሽፈራው አባቡ የወጣቷን ተግባር አድንቀዋል።
ወጣት ጤናዬም በበኩሏ “የእኛ ያልሆነን ማንኛውንም ንብረት መጠቀም በህላችን ስላልሆነ ለባለንብረቱ መመለስ ስላለብኝ መልሻለሁ “ብላለች፡፡
በተጨማሪም “ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የወጣቷን ታማኝነትና ተሞክሮ ሊወስድ እንደሚገባ“ ሀላፊው ተናግረዋል ፡፡