በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የፀረ ሙስና ቀንን ተከበረ፡፡
*******************,,,,
የድህነት በሽታና እንደሀገር አክሳሪ መሆኑን በመገንዘብ ሙስና ጠል ትውልድ እንዲፈጠር በማሰብ አገልግሎቱ በዓሉን አክብሯል፡፡ በአሉን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት ትልቁ ሙስና የገንዘብ ብቻ ሳይሆን የአገልግሎት አሰጣጥና የአሰራር ወገንተኝነተን ያካተተ በመሆኑ ሁላችንም ህዝብን ስናገለግል በተሰማራንበት የስራ ድርሻ ሙስና የሀገርን ኢኮኖሚ የትውልድን ራዕይ የዜጋን ስነ ምግበር የሚያቀጭጭ መሆኑን በማሰብ ሁላችንም ሙስናን መከላከል አለብን ብለዋል፡፡ እንዲሁም የፀረ ሙስናና ስነምግበር መከታተያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራዉ አባቡ በአለም ለ19ነኛ ጊዜ በሀገራችን ለ18ኛ ‹‹ሙስናን መታገል›› በተግባር በሚል መሪ ቃል የሚከበር መሆኑን በማብሰር የሙስናን አስከፊነት በሰፊው አብራርተዋል፡፡
ከሰራተኞች የተነሱ ሃሳብ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን ምላሽ በዋና ዳይሬክተር ምላሽ ተሰቷል፡፡ በመጨረሻም የጥያቄና መልስ ውድድር በማድረግ ለአሸናፊዎች የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት በኣሉ በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡