PSTS

“ኢትዮጵያ…ዘላቂ ሰላማችንን ገንብተን በእኩልነትና በአንድነት የምንኖርባት ሀገር ናት፡፡” ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ

የብዙዎች ሀገር ናት፡፡ የሺ ዓመታት ደማቅ ታሪክ ያላት የአብሮነታችንና የመቻቻል ሀገር ኢትዮጵያ፡፡ በህብር ቀለማት የደመቀች ህዝቦቿን ያስተሳሰረው ድርብ ገመድ ለዓመታት የፀና የብዙ ሀገራት ተምሳሌት የነበረች የሆነች ሀገር ኢትዮጵያ ፡፡

“የሀገር ውስጥና የውጪ ባላንጣዎቿ ለዓመታት በፅናት የታሰረ በአብሮነት ህያው የሆነ ታሪኳን ለማፍረስ ለወትሮ ጅምሮ ያለመታከት ያለ እረፍት የደከሙባት ግን በጀግኖች ልጂቿ ፅኑ ክንድ እና እሳት ረመጥ የሀገር ፍቅር ወኔ እየተመለከተ እንደታሰበላትና እንደተሰራባት ስራ ያልተበተነች ሀገር በመሆኗ እኮራለን ፡፡ ያ! ሁሉ ችግርና ጦርነት ሲያልፍ ህዝቦቿንም በዘላቂ ሰላም ዳግም ሀገራቸውን በህብረት ሊያቆመው እነሆ ጊዜ ግድ ብሏል፡፡ ያለፈው ነገር አለፈ ፡፡ ዛሬ ስለጦርነት ሳይሆን ስለ ሰላም የምናወራበት ጊዜ ነው፡፡ ጦርነት ለማንምና ለምንም አይበጅም፡፡ ከጦርነት ተጠቃሚ የሆነ ሀገርም ዜጋም የለም ከሰላም ግን ብዙ ይተረፋል፤ ብዙ እሸትና ፍሬ ይታጨዳል፡፡ እናም የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ስናከብር ለዘላቂ ሰላማችን እያሰብን በህብረብሔራዊ አንድነታችን ስለምንገነባት ሀገራችን እያሰብን መሆን ይገባዋል፡፡ እንኳን ለ2015 የብሔር ብሔረሰቦች ቀን አደረሳችሁ፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *