አቶ ተስፋዬ ገዳሙ የደቡብ አገልግሎት መስጫ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ
*********,,,,*********,,,,
“የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ በሀገራችን ልንከላከለው ያልቻልነው ችግር ሆኖ እስካሁን የሚቀጥለው ለህይወት ዋጋ ባለመስጠታችን ነው፡፡ አሽከርካሪ ብዙ የስሜት ህዋሳት ሊኖሩት የሚገባ ዙሪያ ገባውን በትኩረት መመልከት የሚችል ለራሱና ለወገኖቹ የማይተካ ህይወት እንዲሁም ለሀገርና ለድርጅቱ ንብረት ሀሳብና ተቆርቋሪ መሆን ይኖርበታል፡፡ እነዚህን አንኳር ነጥቦች ችላ ያለ ጊዜ አደጋ መድረሱ ሰው መሞትም መቀበሉ አይቀሬ ነው፡፡ “
“ሁሉም ባስ ካፒቴኖቻችንን የምንነግራቸውን እንዲያስተውሉ ለደቂቃም ከሃሳባቸው እንዳይጠፋ የምንፈልገው ነጥብ ይሄ ነው፡፡ ጠንቃቃ ሆነው እንዲያሽከረክሩ ስለ አደጋ አስከፊነት ሁሌም በትራፊክ አባላትና በባለሙያዎች ስልጠና እንሰጣቸዋለን፡፡ ይህም ስለሆነ ነው በ2014 ተቋማችን ባደረገው ውድድር ደቡብ ቅርንጫፍ በቀነሰ የአደጋ መጠን የዋንጫ ተሸላሚ የሆነው፡፡ ይህን ውጤታችንን አስጠብቀን መቀጠል አለብን አደጋ አስከፊ ነው፡፡ ብዙ መስራት የሚችሉ ዜጎቻችንን እያሳጣን ነው ፡፡ የተቋማችን የዜሮ አደጋ ራዕይ ማስቀጠል ይጠበቅብናል፡፡”