ከለሊቱ 10፡30 የደሴ የባህርዳርና የአርባ ምንጭ ተሳፋሪዎቻችን ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት ለጉዞ ዝግጁ ሆነው በመግባት ላይ ናቸው ፡፡ በቀልጣፋ የስምሪት አስተናጋጆች ሻንጣቸው ተጭኖ የወንበር ቁጥራቸውን በትኬቱ መሠረት ተነግሯቸው ተቀምጠዋል፡፡
“የአውቶቡሱ ምቾት ልዩ ነው እውነትም የምድር በራሪ” አሉ አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ ተሳፋሪ በሞባይላቸው በአውቶቡሱ ዋይፋይ በዩቲዩብ ዘና እያሉ ፡፡
“ምቾቱ ልዩ ከመሆኑም ባሻገር ስራዬን እየሰራሁ መሄድ በመቻሌ ደስተኛ ነኝ የኢንተርኔቱ ፍጥነት በጣም ይገርማል፡፡ ቢሮዬ ውስጥ እንዳለሁ ይሰማኛል፡፡” ላፕቶፑን ከፍቶ ስራውን በመስራት ላይ ያለው ሌላው ተሳፋሪ
በሌሊት የገቡት የድርጅቱ የማኔጅመንት አባላት ተሳፋሪውን ምን ጎደለ? ምን ይስተካከል? እያሉ መጠየቅ ጀምረዋል፡፡ “ይበል በዚሁ ቀጥሉ ምቾቱ ለጉድ ነው፡፡” የሚሉ አስተያየቶች ብቻ ይደመጡ ነበር፡፡
ወደ ውቦቹ የሀገራችን ከተሞች ደሴ፣ ባርዳርና አርባምንጭ ከለሊቱ 11፡00 ሰዓት ሁሉም ተጉዘዋል፡፡ ደስ ይላል ደስ ይላል፡፡
selam ticek yet magnet endmchel adrashachun btasawkugne