የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ ያስመረታቸውን ልዩ ሀገር አቋራጭ ኤክስፕረስ አውቶቡሶች በሚኒስትሮች አድናቆት ተቸረው፡፡
ጳጉሜ 2/2014 ዓ.ም በአምራቾች ቀን በኢግዚብሽን ማዕከል በተካሄደበት እለት ኤግዚብሽን ላይ ተሳታፊ የነበረው ድርጅታችን ይዞ ከቀረባቸው አገልግሎቶችና ምርቶቹ መካከል አርቴፊሻል ኢንተለጀንሲ የተገጠመለትና በርካታ ለየት ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ያረፉበትን ልዩ አውቶቡስ ነበረ ፡፡
በእለቱ የክብር እንግዳ በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር በክቡር በአቶ አህመድ ሺዴ የተመራው የሚኒስተሮች ቡድን የትራንስፖርት ዘርፉን በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሯ በክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ መሪነት ጎብኝቷል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ፣የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ፣ከተማ መሬትና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትሮችና በርካታ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተጎበኘው ኤግዚቢሽን ማቀዝቀዣ፣ ዋይፋይ፣ መፀዳጃ፣ የአካል ጉዳተኞች መወጣጫ ሊፍት፣ በርካታ የደህንነት ካሜራዎችና አሽከርካሪው እንዳይዳከም ማሳጅ የሚያደርግ ወንበር የተገጠመለት ልዩ ሀገር አቋራጭ አውቶቡስ ከሚኒስትሮች በጭብጨባ የታገዘ አድናቆት ተችሮታል።
ከዚህም ባሻገር ኤግዚቢሽኑን ለመጎብኘት የመጡ በርካታ አዲስ አበባ ነዋሪዎች ሀገር አቋራጭ አውቶቡሱን ከጎበኙ በኋላ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡