PSTS

“በጎነት ለሀገር ብልፅግና”

“በጎነት ለራስ ነው። በጎነት ለተቋም ነው ።በጎነት ለሀገር ነው፡፡ ሰው በጎ ሲሆን ያለውን ይከፍላል፣ ሰው በጎ ሲሆን ያጣውን ይጎበኛል፣ ሰው በጎ ሲሆን የሌለውን ይረዳል፣ የተከፋውን ያፅናናል፣ የታመመውን ይጠይቃል። ዜጋ በጎ ሲሆን ሀገር በጎ ትሆናለች፣ ብልፅግና ከበጎ ጋር አብሮ አለ ።ሁሉም በጎ ከሆነ ሀገር ከብለፅግና ማማ ላይ ከፍ ትላለች ።ዛሬ ለዚህ ነው ድርጅታችን ካለው ውስን በጀት ላይ ቀንሶ ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች አዲሱን ዓመት በተስፋ እንዲቀበሉ እንኳን አደረሳችሁ በሚል ማዕድ ለማጋራትና የበረከት ስጦታን ለማበርከት የተነሳው” የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ ።

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራነስፖርት አገልግሎት ከልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አስተዳዳር ጋር በመተባባር በወረዳው ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ከ200 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የዓመት በዓል መዋያ በረከትን ሰጥቷል፡፡

“መረዳዳት የኖረ ባህላችን ነው ።እናቶቻችንና አባቶቻችን ያወረሳችሁን የመደጋገፍ ባህልን ነው፡፡ ድርጅታችን ይህን የበዓል ስጦታ ለማበርከት በመቻሉ ደስታ ይሰማዋል” ያሉት ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ “በርቱ ፣ጠንክሩ በሀገራችን ላይ ያንዣበበው አደጋ ሁሉ ተወግዶ መጪው አዲስ ዓመት የደስታና የብልፅግና ይሆናል “ብለዋል፡፡

የወረዳ 10 አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ “ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ላደረገው ስጦታና ድጋፍ በአቅመ ደካሞቹ ዜጎች ስም ምስጋና እናቀርባለን” ብለዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *