በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወነውን የአረንጓዴ ልማት ለመደገፍ ከአገልግሎ ሰራተኞች ጋር ከተከሉት ችግኝ ባሻገር የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሴት ሠራተኞች ብቻ ተሳታፊ የሆኑበት የችግኝ ተከላ ተከናወነ፡፡
በአንድነት ፓርክ በተከናወነውን የችግኝ ተከላ ከአንድ ሺህ በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉን የገለፁት የድርጅቱ የስርዓተ ፆታና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ ወይንሸት ኪዳነማርያም “መትከል ብቻ ሳይሆን የተከልነውን ተንከባክበን ለማሳደግ ቃል ገብተናል“ ሲሉ ገለፀዋል፡፡