PSTS

መሴ ኦያያ!

ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ፣ የብስራት FM መስራችና ባለቤት ጋዜጠኛ መሰለ መንግስቱ (መሴ) ወደ ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ጎራ ብሎ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝቷል፡፡

በተለይ በቅርቡ ልዩ ሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ለመስጠት ተመርተው ዝግጁ የሆኑ አውቶቡሶችን የጎበኘው ጋዜጠኛ መሰለ መንግስቱ በሰለጠኑት ሀገራት ያያቸውን ማቀዝቀዣ፣ መፀዳጃ፣ቻርጀርና ዋይፋይ እንዲሁም አርቴፊሻል ኢንተለጀንት የተገጠመላቸውን አውቶቡሶች መጎብኘት በመቻሉ እጅግ እንደተደሰተና ኩራት እንደተሰማው ገልጿል፡፡

“በተለይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ካሜራዎችና ቴክኖሎጂዎች መጠቀሙ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግሮ ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በመልካም ተሞክሮነት ቢወሰዱት በሀገራችን በተሸከርካሪ አደጋ የሚጠፋውን የሰው ህይወት ለመታደግ ይረዳል “ብሏል፡፡

የድርጅቱን የአሽከርካሪዎች ማዕከል፣ የሰራተኛ ልጆች ማቆያ ዴይ ኬር ና የጓሮ ልማትን የጎበኘው ጋዜጠኛ መሰለ መንግስቱ “በተለይ በብዙ ሀብታም ድርጅቶች ተግባራዊ ሆኖ ያላየሁትን ሰራተኞች የስፖርት ማዘውተሪያ ጅምናዚየም በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ተግባራዊ ሆኖ በማየቴ አገልግሎቱ ለሰራተኞቹ የሚያስብና ቅድሚያ የሚሰጥ ብዙ አዳዲስ አሰራሮች በመቀየስ ከሚያውቃቸው በርካታ ድርጅቶች ለየት ብሎ እንዳገኘው” ገልጿል፡፡

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ከድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ከወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ እና ከም/ዋና ዳይሬክተሩ ከአቶ አበባው ልየው ጋር ባደረገው ውይይት “ተቋም መሪውን ይመስላል፡፡ የተመለከትኳቸው አዳዲስ አሰራሮች አመራሩ ሰራተኛውን በማስተባበር ብዙ እንደሚደክም ያሳየኝ ነው ድርጅቴ ብስራት FM101.1 እነዚህን የድርጅቱን ምርጥ ተሞክሮዎች ለማስተዋወቅ ከልብ ይሰራል፡፡” በማለት ያለውን አድናቆት ገልጿል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *