PSTS

የሚኒስትሮቹ ጉብኝት

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡

በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ ማብራሪያ የተጀመረው የሚኒስቴሮቹ ጉብኝት በተለይ በቅርቡ ተመርተው አገልግሎት መስጠት የሚጀምሩትን ልዩ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች ጎብኝተዋል፡፡

“ልዩ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶቹ በተለይ አደጋን ተከላክሎ ለማሽከርከር የሚያስችሉ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው ፣አሽከርካሪው ለአደጋ የሚያጋልጡ ተግባራት ሲፈፀሙ ቀጥታ ለተቆጣጣሪው አካል ሪፖርት የሚያደርጉ መሆናቸው ለየት እንደሚያደርጋቸው ገልፀው ለተሳፋሪው ምቾትን የሚያላብሱ መጸዳጃ ቤት፣ ዋይፋይ በየመቀመጫው ሞባይል ቻርጀር ያላቸው፣ ሰፊ ዕቃ መጫኛና ለአካል ጉዳተኞች ሊፍት የተገጠመላቸው” መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የድርጅቱ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ በሚኒስትሮቹ የተጎበኘ ሲሆን ማዕከሉም አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከር ክህሎት የተካኑ በትክክለኛው መንገድ “ማሽከርከርን ክቡር ሙያ ነው “ብለው የሚያምኑ አሽከርካሪዎችን ለማፍራት ሰልጣኞችን በመቀበል ላይ እንደሆነ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሯ ሌሎች የተቋሙን እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ክቡር አቶ ደንጌ ቦሩ በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር የሎጀስቲክስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በርዖ ሀሰን የትራንስፖርት ዘርፍ ሚኒስተር ዲኤታ ባዩት አዳዲስ አሰራሮችና የስራ እንቅስቃሴ መደሰታቸውን ገልፀው” የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ለሌሎች ተቋማት አርአያ የሚሆን በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው” ብለዋል፡፡

የሰራተኞች የስፖርት ጂምናዚየም ፣ሰራተኞች ልጆች ዴይኬር፣ የጓሮ አትክልት ልማትና የተሸከርካሪ ጥገና ማእከል በሚኒስትሮቹ ጉብኝት ከተካተቱት መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *