PSTS

“የሰው ወርቅ አያደምቅ”

ጠዋት በማለዳ ባስ ካፒቴን ሳሙኤል ተስፋዬ የጎን ቁጥር 5071 እያሽከረከሩ በርካታ የፐብሊክ ሰርቪስ ተሳፋሪዎችን አሳፍረው ከሱሉልታ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ነበሩ፡፡

በእለቱ መምህር ታደሰ ጌታቸው ወደ ሚያስተምሩበት ፀሐይ ጮራ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩትን ትምህርት በመንገድ ላይ እየከለሱ ተጉዘው ትምህርት ቤታቸው ደረሱና ወረዱ፡፡ ግን ሞባይላቸውን ከኪሳቸው ሲፈልጉት የለም፡፡ “ከመደንገጤ የተነሳ የት እንደጣልኩት ለመገመት እንኳን ተቸግሬ ነበር፡፡ ስልኩስ ይገዛል ውስጡ ያለው መረጃ ቆጨኝ፡፡ ሌባ እንደሰረቀኝ ገምቻለሁ፡፡” ይላሉ መምህር ታደሰ

ወዲያው የአውቶቡሱ አስተባባሪ በሌላ ሰው ስልክ ደውሎ የአውቶቡሱ አሽከርካሪ ስልኩን እንዳገኙት እንደገለፁለትና መጥተው መውሰድ እንደሚችሉ ተነገራቸው፡፡

“በጣም ደስ አለኝ፡፡ የአውቶቡሱ ሹፌር ምንም ነገር ሳያጓጓው ወዲያው ደውሎ ንብረቴን መመለሱ እጅግ አስደስቶኛል፡፡ በመምህር ደመወዝ ደግሞ በቀላሉ ሞባይል መግዛት አልችልም ነበር፡፡ ባስ ካፒቴን ሳሙኤል ላደረጉልኝ ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ አውቶቡስ አሽከርካሪዎቹ ታማኞች የተከበሩ ናቸው፡፡ ሲባል እሰማ ነበር፡፡ ዛሬ እኔም እማኝ ነኝ፡፡ ታማኝነት ያኮራል፡፡ ራስንም መስሪያ ቤትንም ያስጠራል፡፡ ኪስ ገብቶ የሚሰርቅ እንዳለ ሁሉ ከኪስ የወደቀን ፈልጎ የሚሰጥ ታማኝ ሰው አለ፡፡ ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትን እጅግ አመሰግናለሁ፡፡”

መምህር ታደሰ ጌታቸው፡፡

“የሰው ወርቅ አያደምቅም፡፡ ይህ ሞባይል የሰው ሀብት ነው፡፡ የሚገባው ለባለቤቱ ብቻ ነው፡፡ አያስገርምም፡፡ የሰው ንብረት አገኘሁ ለባለቤቱ መለስኩ፡፡ ነገም ይህን ተግባሬን እቀጥላለሁ፡፡ ሁላችን ባስ ካፒቴኖች በዚህ ጉዳይ ላይ ያለን አቋም አንድና አንድ ነው፡፡ የሰው ወርቅ አያደምቅ” ባስ ካፒቴን ሳሙኤል ተስፋዬ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *