PSTS

ክብርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ብሔራዊ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ማስተግበሪያ ስርአትን ተመለከቱ፤

አዲስ አበባ ሰኔ 3 ቀን 2014 ዓ.ም፡ በቅርቡ ተግባራዊ የሚሆነውን ብሔራዊ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓትን የሚያግዘው ማስተግበሪያ በተሽከርካሪዎች ላይ የሙከራ ትግባራ ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በአዲስ አበባ በፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት የከተማ ታክሲ አገልግሎት በሚሰጡ ተሽከርካዎች ላይ የብሔራዊ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ስርዓት ማስተግበሪያን ተግባራዊ የስራ ሂደትን ተመልክተዋል፡፡

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚንስቴርና በኢትዮ ቴሌኮም የበለፀገው መተግበሪያው በቴሌ ብር አማካኝነት የተቀላጠፈ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ ሲሆን የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች በቀላሉ በነዳጅ ማደያ ተገኝተው አገልግሎት የሚያገኙበት ቴክኖሎጂ ነው፡፡

በመላ ሃገሪቱ የታለመ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሚሆኑ ከ2 መቶ ሺ በላይ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ይህን መተግበሪያ ያለምንም እንከን መጠቀም የሚችሉበት ደረጃ ላይ መሆኑን ክብርት ሚንስትር ዳግማዊት ሞገስ በሙከራ ትግበራ ሂደቱ ተመልክተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *