የሚሰሙ ዜናዎች ሁሉ ያማሉ ፡፡ በተለይ ጠዋት በማለዳ በራዲዮ የሚሰማው ዜና የሞት መርዶ ከማስደንገጥ አልፎ በመንገድ ላይ ለመጓዝ ያስፈራል፡፡ የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ዜጎቻችንን በየመንገዱ እያስቀረ ነው፡፡ጨቅላ ህፃናትን ከነደብተራቸው፣ አውንቶችን ከነበትራቸው ፣ጉሊት ነጋዴዎችን ከነሸቀጣቸው ፣ዘናጩንም ባመረ መኪናው ከነከረቫቱ ….. ሁሉም እንደወጣ ይቀራል፡፡
“ለምን ብለን ስላልጠየቅን ወይም አይተን እንዳላየ ስለሆንን ይህ መአት እየወረደብን ነው፡፡ ሰርተው ለሀገርና ለመወገን መጥቀም የሚችሉ ዜጎች እንደወጡ ይቀራሉ ፡፡ ቤተሰብ እየተበተነ ፣ጎጆ እየተዘጋ ፣ትዳር እየተበተነ ነው፡፡ በመጠንቀቅ በማስተዋል ልንከላከለው እንችላለን። አደጋን ተከላክለን ብናሽከረክር ወገኖቻችንን ከሞት ዜጎቻችንን ከአካል ጉዳት እናድናለን። ይቻላል፡፡ ሁሌም አደጋ ሊደርስ እንደሚችል እያሰቡ መጠንቀቅ መልካም ነው ።ጎበዝ እንጠንቀቅ፡፡ እኛ ለስድስት ዓመታት አዲስ አበባ ውስጥ ሽንጣሙን የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡስ ስናሽከረክር ጭረት እንኳን አደጋ አልደረሰብንም፡፡ በመሆኑም አደጋን ዜሮ ማድረግ እንደሚቻል በተግባር አረጋግጠናል፡፡ እባካችሁ ልጆቻችሁን ፣እናቶቻችሁን አባቶቻችሁን ወገኖቻችንን ከመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ጠብቁ … እንደሚቻል እኛ ምስክር ነን” ባስ ካፒቴን ታጠቅ ነጋሽ እና ባስ ካፒቴን አብደላ ኑሪ ለስድስት ዓመታት ያለአደጋ ያሽከረከሩ የባስ ካፒቴኖቻችን መልእክት።እናስ እርስዎ አሽከርካሪው ምና ያስባሉ?