የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ አባላት በድርጅቱ ውስጥ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ ፡፡
ለቦርድ አባላቱ የሚያዝያ ወር የስራ አፈፃፀምን በተመለከተ ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን የወሩ አፈፃፀም በከፍተኛ ሁኔታ የተከናወነ መሆኑን ገምግመዋል፡፡
የስራ አመራር ቦርድ አባላቱ ድርጅቱ የስራ አካባቢን ምቹ ለማድረግ እያደረገ ያለውን ጥረት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ገንቢ አስተያየታቸውንም ሰጥተዋል።
የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ፣ የሠራተኞች የጨቅላ ህፃናት ማቆያ ፣ የስፖርት ጅምናዚየም፣ የሰሌዳ ምርት ክፍልና እደላ በስራ አመራር ቦርድ አባላቱ ከተጎበኙበት የስራ ክፍሎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከማቋቋም ጀምሮ ባለውለታ የሆኑትና የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በዛብህ ወ/የስ “ድርጅቱ ዘወትር በለውጥ ጎዳና ላይ ነው። ሁሌም አዲስ ነገር ሁሌም ለውጥ የሚያሳይ ለብዙ ተቋማት ምርጥ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ድርጅት ነው፡፡” ብለዋል፡፡
ሰብሳቢው አያይዘውም “ዓመቱን በበለጠ ውጤት አጠናቀን ቀጣዩ 2015 እጅግ በላቀ ውጤት ለመጨረስ ከወዲሁ የተጀመረው ዝግጅት ተሞክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ ባየነው ነገር ሁሉ እጅግ ደስተኞች ነን” ብለዋል፡፡