PSTS

እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ2014 በጀት ዓመት የ10 ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

አዲስ አበባ ግንቦት 19 ቀን 2014፡ ሪፖርቱን ለተከበረው ምክር ቤት ያቀረቡት የትራንስፖርና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የዘርፉን ዋነኛ ተልዕኮ ከማሳካት አኳያ ባለፉት አስር ወራት የተከናወኑ የቁልፍ እና አበይት ተግባራት አፈፃፀምን በዝርዘር አቅርበዋል፡፡ በትራንስፖርተና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የሎጂስቲክስ ዘርፍ፣ የባቡር ትራንስፖርትና የአቪዩሽን ዘርፍን በተመለከተ ለተከበረው ምክር ቤት ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ክብርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ጥራት ያለው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መስጠት ለእኛ ግዴታ ለህዝብ ደግሞ መብት ነው ያሉ ሲሆን አገልግሎት አሠጣጥን ለማዘመን በአስር ወሩ ውስጥ በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን አንስተዋል፡፡ ለአብነትም በጭነት ትራንስፖርት ላይ የተገኘውን ስኬት አንስተው በመናህሪያዎች ላይም ለመድገም እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ አብዛኛው ህብረተሰብ የሚገለገለው በመናህሪያ በመሆኑ በቃሊቲ እየተገነባ የሚገኘው መናህሪያን ሞዴል በማድረግ ዘመናዊ መናህሪያዎችን የመገንባት ስራ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡ በ2014 በጀት ዓመት የ10 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርታቸው በሀገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት 417.1 ሚሊየን ተሳፋሪዎችን በማጓጓዝ የዕቅዱን 91 ከመቶ ማሳካት መቻሉን፣ በገቢና ወጪ ጭነትት 11.09 ሚሊየን ቶን ዕቃ መጓጓዙን፣ በሎጂስቲክስ ዘርፍ እቃዎችን በኮንቴነር አሽጎ መላክ በመቻሉ ከ105 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ማዳን ስለመቻሉ፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም 69 በመቶ ማደጉን አካተዋል፡፡ለተቋማዊና ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የጠቀሱት ክብርት ሚንስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የ30 ዓመት የትራንስፖርት ማስተር ፕላን በማዘጋጀት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ጠቅሰዋል፡፡ የአቅም ግንባትን በማጠናከር፣ የክትትልና ግምገማ ሥርዓትን በማዳበር፣ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን በማሳደግ ዘርፉን ወደተሻለ ውጤት ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡የተከበረው ምክር ቤት አባለት የ30 ዓመት የትራንስፖርት ማስተር ፕላን መዘጋጀቱን ፤ በሎጂስቲክስ ዘርፍ ወጪ መቀነስ መቻሉን አድንቀው በበጀት አመቱ 10 ወራት የተከናወነው አጠቃላይ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን በማንሳት የምክር ቤቱ የከተማ መሠረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የተከበረው ምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተው በክብርት ሚንስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *