የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በቅርቡ ከድርጅቱ ሠራተኛ ማህበር ጋር ባደረገው ምክክርና ውይይት ስራ ላይ ተሸሽሎ በዋለው የህብረት ስምምነት ዙሪያ ለደቡብና ሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሰራተኞች የግንዛቤ ማዳበሪያ ውይይት አደረገ፡፡ቀደም ሲል ይታዩ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በማረምና ለሠራተኛው ጥቅም የሚሰጡ እንዲሁም ድርጅቱን ወደ ላቀ ደረጃ ይደርስ ዘንድ የሰራተኛውን ተሳትፎ ለማጎልበት ሀሳቦች በተካተቱበትና በተሻሻለው የህብረት ስምምነት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡