በሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ በሚፈለገው መጠን ሊቀንስ ያልቻለውን የመንገድ ላይ የተሸከርካሪ አደጋ በድርጅቱ ውስጥ ለመቅረፍ የሚያስችል የጋራ ምክክር በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ተካሂዷል፡፡በዘርፉ ልምድ ባላቸው የአዲስ አበባ የትራፊክ ፖሊስ በመጡ አባላት በተመራው ውይይት ላይ ከሰሜንና ከደቡብ ቅርንጫፍ የተወጣጡ ባሰ ካፒቴኖች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ በውይይቱም ወቅት አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከር በአደጋው የሚደርሰውን ሞትና የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት እንዴት መከላከል እንደሚቻል ትምህርታዊ ገለፃ ተሰጥቷል፡፡