PSTS

ታማኝኘት ባህላችን ሆኖ ቀጥሏል

በልደታ ክፍለ ከተማ የሃይማኖት ተቋማት ቡድን መሪ ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው አቶ ሰለሞን ገበየሁ ግንቦት 4 /2014 ዓ.ም ስራ ውሎ ወደ ቤቱ ለመሄድ ከአየር ጤና የጎን ቁጥሩ 8073 በሆነው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት አውቶቡስ ጉዞ ይጀምራል፡፡ “ስሰራ ውዬ ደክሞኝ ነበር ሌሎች ዕቃዎችን ይዤ ስለነበር ላፕቶፕ የያዘ ሻንጣዬን አውቶብስ ውስጥ ጥዬው ወረድኩ፡፡ ጥዬው መውረዴን ያወኩት ከሰዓታት በኋላ ነበር፡፡ ዕቃ እንደጠፋብኝ የነገርኳቸው የስራ ባልደረቦቼ ሌላ ቦታ ካልጣልከው አውቶቡስ ውስጥ ከሆነ ባስ ካፒቴኖች ታማኞች ስለሆኑ በእርግጠኝነት ታገኘዋለህ ብለው ተስፋ ሰጡኝ” ይላል አቶ ሰለሞን፡፡“እውነትም እንደተባለው ታማኙ ባስ ካፒቴን ነጋሽ ቦጋለ ከላፕቶፑ ተጨማሪ የባንክ ቡክና ATM ያለበትን ሻንጣ በክብር አስረክበውኛል፡፡ ነጣቂ በበዛበት ጊዜ እነዚህን የመሰሉ ታማኝ አባት ባስ ካፒቴን መገኘታቸው ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት እጅግ በጣም እናመሰግናለን፡፡” በማለት የጠፋበትን ዕቃ ተረክቧል፡፡ “ታማኝነት ለራስ ነው። ማንም በማንም ገንዘብ ከብሮ አያውቅም፡፡ እኛ መስሪያ ቤት ይህ ታማኝነት ባህል ነው፡፡ አውቶቡስ ውስጥ የተረሳ ዕቃ ጠፍቶ ቀርቶ አያውቅም፡፡ ድርጅታችን በኛ እንዲኮራ እንጂ እንዲያፍር አናደርግም፡፡ ስለዚህ ንብረቱን ለባለቤቱ በማስረከቤ ክብሩ ለኔ፣ ለመስሪያ ቤቴና ለቤተሰቦቼ ነው፡፡ ይኽን በማድረጌ እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ መስሪያ ቤታችን ሁሌም የሚሰጠን የስነምግባር ስልጠና እጅግ ጠቅሞናል፡፡ በቀጣይም ሁላችን በዚህ ታማኝነታችን እንቀጥላለን፡፡ የድርጅታችን ዝናና ክብር ከፍተኛው ነው፡፡ ይህን የሚመጥን አገልግሎት ሁሌም ለመስጠት ተግተን እንሰራለን” ባስ ካፒቴን ነጋሽ ቦጋለ፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *