PSTS

ERP የማስጀመሪያ መርሃ ግብር

የድርጅቱን አጠቃላይ ስራ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አሰራር ለማዘመን የሚያስችል ERP /Enterprise Resource planning/ አተገባበርን በስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተከናወነ፡፡የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ኤክሲድ ከተባለው ድርጅት ጋር በገባው ውል መሠረት የድርጅቱን አጠቃላይ አሰራር ወደ ላቀ የቴክኖሎጂ አተገባበር የሚያሳድግና ስራቸው ግድ ከሚላቸው የስራ ሂደቶች በስተቀር ወረቀት አልባ አሰራርን እውን የማደረግ አብይ አላማ አለው፡፡የማስጀመሪያ መርሃ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የድርጅቱን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር “ጊዜና ገንዘብ ቆጥቦ ስራን በጥራትና በዘመናዊ መልኩ በፍጥነት ማከናወን ድርጅቱን የላቀ ተወዳዳሪ ከማድረግ ባሻገር የሚያስገኘውን ጥቅምና ትርፍ ሁለንተናዊ ነው” ካሉ በኋላ “ውል የያዘውን ኤክሲድ ድርጅቱ ከተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ባነሰ ሰርቶ ያስረክበናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ድርጅታችን ይህ ዘመናዊ አሰራር ተግባራዊ እንዲደረግ ምሽትና እረፍት ቀናችንንም በመተቀም ከኛ የሚያስፈልገውን ማንኛውም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን” ብለዋል፡፡ከኤክሲድ ድርጅት የመጡ የስራ ኃላፊዎችም አጠቃላይ የስራ ሂደቱን አስመልክተው ለድርጅቱ የማኔጅመንት አባላት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *