በድርጅታችን በአራቱም ቅርንጫፍ ያሉ ክፍት ቦታዎች ጦም እንዳያድሩ ተደርገዋል፡፡ መሬቱን ለጓሮ እርሻ ተስማሚ እንዲሆን አድርጎ ያስተካከለው ሠራተኛው ነው፡፡ መትከልና ማረም ሁሌም የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖረተ ሠራተኛው ስራ ነው፡፡ እናም ጎመን ፣ሰላጣ ፣ድንች ቲማቲም ወ.ዘ.ተ ደርሶ ከጓሮ እሸት እየተለቀመ መልሶ ለሰራኛው ይታደላል፡፡ምርቱም ለሰራተኛው ክበብ እየቀረበ በአነስተኛ ዋጋ መልሶ ለሰራተኛው ይሸጣል፡፡ በቅርንጫፎች መካከልም ፉክክሩ የጦፈ ነው፡፡ “እውነት ግን ብዙ ቦታዎች ጦም እያደሩ ቢያንስ ሌላ ቢቀር የጓሮ አትክልት እንዴት እንቸገራለን፡“፡ ብሎ መጠየቅ አብይ አጀንዳ ነው፡“ክረምቱ በሙሉ አቅሙ ሲገባ ምርታችን በእጥፍ ይጨምራል፡፡” እያሉ ነው የየቅርንጫፉ ስራ አስኪያጆች ፡፡ “ዘወትር እሸቱ በትኩሱ ተቀጥፎ ለሰራተኞቹ ይታደላል፡፡” “ከጓሮ እሸት ቀጥፎ በእጅ ይዞ ነው እንጂ” እንዲል ንዋይ ደበበ