PSTS

ታማኙ ባስ ካፒቴን

ወጣት ኪሩቤል ጉታ ይባላል፡፡ የወረዳ 8 ሚሊኒየም ጤና ጣቢያ ባለሙያ ነው፡፡ እንደተለመደው ሁሉ ወደ ቤት ለመሄድ የሚጠቀመውን የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡስ የጎን ቁጥር 6053 አውቶቡስ ይዞ አርብ መጋቢት 23/2014 ወደ ቤቱ ይጓዛል፡፡ “የኛ ስራ እንደሚታወቀው አድካሚ ነው። በዕለቱ ደክሞኝ ነበር ላፕቶፔንና ሌሎች ንብረቶችን መቀመጫው ላይ እንዳደረግሁት ሳር ቤት ጥየው ወረድኩ” ይላል የጤና ባለሙያው ኪሩቤል ጉታ።ድንገት አውቶቡሱን የፈተሹት ባስ ካፒቴን በርካታ የመስሪያ ቤትና የግል መረጃ የያዘውን ሞባይል ልብስና አጀንዳ ያገኛሉ ፡፡ ከአውቶቡስ አስተባባሪው ጋር በመሆንም ንብረቱን መዝግበው በመያዝ ባለቤቱን ፍለጋ ይጀምራሉ፡፡“የሰው ንብረት የሰው ነው ፡፡ ኮምፒዩተሩ ብዙ ጠቃሚ መረጃ እንዳለው ስለገመትኩ ለመስሪያ ቤቴ አሳወቅሁ፡፡” ይላሉ ባስ ካፒቴን አስፋው በቀለ“ብዙ የግልና የድርጅቱ መረጃ የያዘ ላፕቶፕ ነው፡፡ የፐበረሊክ አውቶቡስ ሾፌሮች በዕድሜ ተለቅ ያሉና ጨዋዎች መሆናቸውን ስለማውቅ እነሱ ካገኙት ይጠፋል ብዬ አልገመትኩም ነበር።ግምቴም ትክክል ሆኖ ንብረቴ ምንም ሳይሆን ተገኝቶልኛል፡፡ ለጨዋው ባስ ካፒቴን ዕድሜ ይስጥልኝ እላለሁ፡፡ እንደዚህ መሰል ታማኝ ሰራተኞች ላሉት የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በጣም ምስጋናዬን ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡” ሲል ወጣት ኪሩቤል ንብረቱን በተረከበበት ጊዜ ተናግሯል፡፡ “የድርጅቴ ስም እንዲህ በመልካም ሲጠራ መስማቴ አስደስቶኛል፡፡ ብዙ የስራ ባልደረቦቼም ቀደም ሲል ወርቅ፣ ብርና ዶላር አግኝተው ለባለቤቶቹ በታማኝነት አስረክበዋል፡፡ ይህ የእኛ በመስሪያ ቤት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ የሰው ገንዘብ ለባለቤቱ እንጂ ላልደከመበት ሰው ገንዘብ አይሆንም ።ንፁሁንም ገንዘብ ይዞ ይጠፋል፡፡” ባስ ካፒቴን አስፋው በቀለ፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *