የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የማኔጅመንት አባላት ከአገልግቱ ሠራተኞች ጋር አጠቃላይ የስራ ውይይት አካሄዱ ፡፡ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ “ድርጅቱ በየጊዜው ለሚያገኘው የአገልግሎት ጥራት ሽልማትና ከተጠቃሚው ለሚሰጠው በጎ ምላሽ አጠቃላይ የድርጅቱ ሠራተኞች በተለይ ደግሞ ከትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የሚያደርጉት ባስ ካፒቴኖችና የአገልግሎት ክፍያ ተቀባዮች ከፍተኛ ድርሻ አላቸው፡፡” ካሉ በኋላ “በ2014 የበጀት አመት የያዝናቸውን ዕቅዶች የምናጠናቅቅበት ወራት በመሆኑ ዓመቱን እንደተለመደው በስኬት ለመጨረስ የቀሩን ስራዎች ካሉ ፈትሸን ማጠናቀቅ ይኖርብናል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በውይይ ላይ የተሳተፉ ሰራተኞችም በጠንካራ ጎን ያነሷቸው ሀሳቦች እንደተጠበቁ ሆነው ሊስተካከሉ ይገባል ያሏቸውን አስተያየቶችና ጥያቄዎች አንስተዋል፡፡ የማኔጅመንት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ውይይቱን በንግግር አጠቃለዋል፡፡