የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርተ አገልግሎት ድርጅት የሚፈጠሩ የተሸከርካሪ አደጋዎችን አደጋን ተከላክሎ የማሽከርከር ስልጠና ከአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ለባስ ካፒቴኖች (ለአውቶቡስ አሽከርካሪዎቻችን) ሰጠ፡፡ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የትራንስፖርት ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ፉፋ “ድርጅቱ የዜሮ አደጋ ራዕይ ተግባራዊ የሚሆነው የመንገድ ላይ ህግና ደንብን በማክበር በመሆኑ ሁሌም መወያየት መነጋገርና ግንዛቤን ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም ከድርጅቱ ጎን በመቆም ለባስ ካፒቴኖቻችን ስልጠና እየሰጠና እየደገፈን ያለው የአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ጽ/ቤት እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡» አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር የመንገድ ላይ ትራፊክ ህግና ደንብ የአሽከርካሪ ስነ ምግባር……. በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ለአራቱ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባስ ካፒቴኖች ስልጠና የሰጡት ኢ/ር ሰለሞን በከተማው ውስጥ ካለው የተሸከርካሪ አደጋ ጋር በማጣመር ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡የድርጅቱ የዘጠኝ ወራት የተሸከርካሪ አደጋ ትንተናም በአቶ ታዬ ታምሩ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡