በሀገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የተሸከርካሪ ሰሌዳ አሰጣጥና ምትክ ማውጣት ስርተን ወጥና የተሳለጠ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ ፡፡የተሸከርካሪ ሰሌዳ መስጠትን ከትራንስፖትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በውክልና ወስዶ በማከናወን ላይ ባለው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በተዘጋጀውና የክልል ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ በሆኑበት የቪዲዮ ኮንፍረስ ላይ የሰሌዳ አምርቶ መስጠት ከጀመረበት ከህዳር 2014 – መጋቢት 2014 ድረስ ክልሎች ምን ያህል ሰሌዳ ጠየቁ ?ምን ያህል ተመረተ? ምን ያህሉ ለክልሎች ክፍያቸውን አጠናቀው ወሰዱ ?ምን ያህል ሳይወስዱ ቀሩ?…. በሚልና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ ለኃላፊዎቹ ስራ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ከአስተዳዳሮችም ሆነ ከክልል ቢሮዎች ምትክ ሰሌዳ በሚስፈልግበት ጊዜ ተመሳስለው ከሚሰሩ ሀሰተኛ ማስረጃዉች የተጠበቀና ከወንጀል የፀዳ ለማድረግ የትራንስፖርት ቢሮዎች ለሚሰጡት ማስረጃ ኃላፊነት መውሰድ እንዳለባቸውና ከፖሊስና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ወንጀሉን ለመከላከል የበኩላቸውን መወጣት እንደሚገባቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡በመጨረሻም የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በሰጡት ማጠቃለያ “የተሸከርካሪ ሰሌዳዎች እንዲመረትላቸው አዘው ምርቶቹን አስፈላጊውን የክፍያ መስፈርት አሟልተው መውሰድ ሲገባቸው ያልወሰዱ ቢሮዎች ባስቸኳይ ምርቱን እንዲረከቡ አሳስበው የ2015 የፍላጎት ዕቅዳቸውን ሰርተው እንዲልኩ” ለቢሮ ኃላፊቹ ገልፀውላቸዋል፡፡