PSTS

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ሁለተኛዉ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ አፈፃፀም ተገመገመ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የ2014 በጀት ዓመት ሁለተኛዉ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ በየተቋማቱ ዋና ዳይሬክሬክተሮች በዝርዝር ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በመደረኩ ላይ ተገኝተው በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሻለ ውጤትን ለማረጋገጥ ሰራዎችን ከምንግዜም በላይ በጥልቀት በመገምገም እንዲሁም ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ልንሠራ ይገባል ብለዋል፡፡ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ መሠረተ ልማት የማሰፋፋት ስራዎች ፣ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽነትን የማሻሻል ፣ የጭነት ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት የገቢ ዕቃዎችን የወደብ ላይ ቆይታ (Port Dwell time) የመቀነስ ፣የ3ኛ ወገን መድን ሽፋንን ማሳደግ ፣በሃገር አቀፍ ደረጃ የተቀናጀ የመንገድ ትራፊክ ቁጥጥርና ህግ የማስከበር እንዲሁም የፐብሊክ ሰርቪስ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር ማሳደግ፣ በአቪዬሽን ዘርፍ የተሻሻለና ተደራሽ የሆነ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት የመሰጠት ሰራዎች የ2ተኛው ዙር 100 ቀን እቅድ አፈጻፀም ላይ በትኩረት የተሰሩ ሰራዎቸ መሆናቸዉ ተገምግመዋል:: በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የ2ተኛው ዙር 100 ቀን እቅድ አፈጻፀም ላይ የተሰሩ ሰራዎቸ አበረታች መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ በዘርፉ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቅንጅት ሊሠራ እንደሚገባ ገልፀዉ በትኩረት ሊሠሩ በሚገባቸዉ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር የሰራ መመሪያ አሰቀምጠዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *