PSTS

የተግባቦትና የደንበኛ አያያዝ ስልጠና

ለፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሰራተኞች የተግባቦት ክህሎትን ለማሳደግና የደንበኞች አያያዝ በተመለከተ የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጠ ፡፡በቀን ከ100 ሺህ በላይ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን የማያስተናግዱ ባስ ካፒቴኖች በሰነምግባር ደንበኞችን እንዲይዙና እንዲያስተናግዱ የሚረዳው ስልጠና በተግባቦት ጥበብ ካልታገዘ ውጤት አልባ በመሆኑ ሁለቱን ርዕሶች በማጣጣም ስልጠናው እንደተሰጠ የገለፁት ስልጠናውን የሰጡት የድርጅቱ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን አምባቸው ስልጠና ተግባራዊ መደረጉን በመስክ ምልከታ እንደሚረጋገጥ ለሰልጣኞቹ ገልፀዋል፡፡ “ተግባቦት የህይወት መሠረት ነው የተግባቦት ጥበብን የተረዳ ሰራተኛ በደንበኛ አያያዝ የተካነና ምስጉን ይሆናል ፡፡ በአገልጋይና በተገልጋይ መካከል ሊኖር የሚገባን የተግባቦት ዕውቀት መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ ለውጤት ስለሚያበቃ ይህ ስልጠና ተዘጋጅቷል፡፡” ያሉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ “ከስልጠናው ያገኛችሁትን ጠቃሚ ዕውቀት በተግባር በመተርጎም የድርጅታችንን የደንበኛ ዕርካታ ከነበረበት ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር አለባችሁ”ሲሉ ስልጠናውን በንግግር ዘግተዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *