የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ111 ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ46 ጊዜ የተከበረውን ማርች 8 ከሰራተኞች ጋር አከበረ።”እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል ተከበረውን ቀን በንግግር የከፈቱት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት ትልቁ “ከዚህ በበለጠ ትግል ሴቶች አሁን ካለው የሴት አመራሮች ቁጥር በልጠን መታየት አለብን።ለዚህም በተሰማራንበት የስራ መልክ ውጤታማ መሆን አለብን”ብለዋል።