PSTS

የክልል መለያን የያዙ ሰሌዳዎችን የሚያስቀር ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሠራጨ ያለዉ መረጃ የተሳሳተ ነዉ፡፡

4ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ ላይ አስፈላጊዉን ግብዓቶችን በማካተት እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መምራቱ ይታወሳል፡፡ሆኖም ግን ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ዉጭ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የክልል መለያ ከተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ መመራቱን የሚገልጽ ዜና እየተዘገበ ስለመሆኑ አረጋግጠናል፡፡በመጀመሪያ መረጃዉ የተሳሳተና ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ዉጭ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ በመቀጠልም በቀድሞ አዋጁ የነበረዉ የተወሰኑ ክልሎችን ታርጋ ዝርዝር የያዘ አባሪ በዚህ ረቂቅ አዋጅ የቀረዉ መንግስት ተጨማሪ ክልሎች ሲወጡ በየጊዜዉ በአዋጁን ማሻሻል ሳያስፈልገዉ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችል ታስቦ መሆኑ ታዉቆ የክልል መለያ ሰሌዳን ከተሸከርካሪዎች ላይ የማንሳት የረቂቅ አዋጁ ሀሳብና ይዘት አካል እንዳልሆን ሊታወቅ ይገባል፡፡ረቂቅ አዋጁ የመንገድ ትራንስፖርትን አስመልክቶ የፌዴራሉንና የክልል አስፈጻሚ አካላት የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር በማያሻማ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ከመሆኑም በላይ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት የመንገድ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጎልበት ዘርፉ አስተማማኝ፤ የተቀናጀ፤ ዘመናዊና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ሆኖ እንዲራመድ የሚያስችል ሲሆን በቅርቡም ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ሰፊ ዉይይት ተደርጎና አስፈላጊዉ ማሻሻያ ተደርጎበት እንደሚጸድቅ ይጠበቃል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *