PSTS

ጉብኝት ተካሄደ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የመስክ ምልከታና ውይይት አካሄዱ ፡፡የተከበሩ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የተመራው ኮሚቴ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በሠራተኛ ወደ ስራ መግቢያ ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የጉዞ አቅጣጫዎች በመገኘት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ከመስክ ጉብኝቱ በኋላ ከድርጅቱ ስራ አመራር አባላት ጋር ጥያቄና መልስ ያደረጉት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በጉብኝታቸው ወቅት የተመለከቱትን ጥንካሬና መስተካከል ይገባቸዋል ያሏቸውን ሃሳቦች አንስተው ምላሽ የተሰጣቸው ሲሆን የድርጅቱ የስራ አመራር አባላት ከቋሚ ኮሚቴው አባላት የተነሱና ሊስተካከሉ የሚገቡ አስተያየቶች በግብአትነት ወስደዋል፡፡ “ድርጅቱ በተለያዩ ዘርፎች እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ ለሌሎች ተቋማትም እንደ ተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባ ነው “ያሉት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ “በተለይ ድርጅቱን እንደ ራዕዩ ሁሉ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ የበለጠ የተጠናከረ ስራ ለሰራ ይገባል፡፡” በማለት የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ “ሁሌም የቋሚ ኮሚቴው አባላት ለድርጅታችን የሚሰጡት አስተያየትና የስራ መመሪያ ለድርጅታችን ስኬት መሠረት ነው፡፡” ያሉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ “ከቋሚ ኮሚቴው አባላት የተሰጡን የጥንካሬ ማበረታቻዎች የራሳችን ስለሆኑ በክፍተት የተጠቆሙትን ለይተን በመስራት ለበለጠ ውጤት ከዛሬ ጀምሮ እንሰራለን” ብለዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *