PSTS

የተሸከርካሪ ሰሌዳን እናስጨርሳለን በማለት ገንዘብ ከሚጠይቁ ግለሰቦች ህብረተሰቡ መጠበቅ እንዳለበት ተገለፀ

የተሸከርካሪ ሰሌዳን ህትመትና ስርጭት ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በውክልና ተረክቦ ስራውን በማከናወን ላይ ያለው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ጉዳይ እናስፈፅማለን በሚል  ገንዘብ ከሚጠይቁ ግለሰቦች መጠንቀቅ እንዳለበት ገለጸ፡፡

የድርጅቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር  አቶ ሰለሞን አምባቸው በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ የተሸከርካሪ ሰሌዳን በህጋዊ መንገድ ከክልልና ከአስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር በመስጠት ላይ መሆኑን ገልፀው የተፈጠረው የህትመት ስርጭት አከናዋኝ የባለቤትነትን ለውጥ በመጠቀም አንዳንድ ግለሰቦች የሰሌዳ ቁጥር የሚፈልጉ አሽከርካሪዎችን ጉዳይ እናስፈፅማለን በማለት የማታለል ተግባር እየፈፀሙ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እነዚህን ወንጀለኞች ለማጋለጥ ድርጅቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመስራት ላይ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ ሰሌዳ ለሚጠይቁ በክልልና በአስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮዎች አማካኝኘት ህጉን ተከትሎ እየሰጠ ነው ሲሉ ምንም ዓይነት የጥሬ ዕቃም ሆነ የህትመት ችግር እንደሌለ ገልፀዋል፡፡

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ስራውን ከመረከቡ በፊት በቀን በአማካኝ 300 የሰሌዳን ቁጥሮችን ይታተሙ እንደነበር ገልፀው በአሁኑ ጊዜ የዕረፍት ቀናትን ጨምሮ በምሽት ክፍለ ጊዜ ህትመትና ስርጭት በመከናወኑ በቀን በአማካኝ ከ3 ሺህ በላይ የተሸከርካሪ ሰሌዳዎችን በመታተም ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጉዳይ እናስፈፅማለን በማለት ገንዘብ የሚጠይቁ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት ህብረተሰቡ ለፖሊስ መጠቆም አለበት ያሉት አቶ ሰለሞን አምባቸው ድርጅቱ በተቀላጠፈና በአጭር ጊዜ በህጋዊ መንገድ የሁሉንም ዓይነት ተሸከርካሪዎች የሰሌዳ ቁጥር እያተመ በማሰራጨት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *