የተነቃቃ፣ ለራሱና ለድርጅቱ ራዕይ መሳካት የድርሻውን ለመወጣት የተዘጋጀ ሰራተኛ መፍጠር ውጤቱ እጅግ የጎላ ነው፡፡ይህን ዕውነታ ተገንዝቦና ቆም ብሎ ህልሙን ለማሳካት የሚጥር አመራና ሰራተኛ መኖር አለበት በሚል ቀደም ሲል ለድርጅቱ ስራ አመራር የተሰጠው Motivational Training ወደ ሰራተኛው ወርዶ “እኛ ድንቅ ነን ድርጅታችን ድንቅ ነው”በሚል ርዕስ ከመቶ ለሚበልጡ ሰራተኞች በታወቀው ባለሙያ በዳዊት ድሪምስ ስልጠና ተሰጥቷ።ልለአንድ ቀን ከግማሽ በተሰጠው ስልጠና ከመቶ በላይ ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ሰልጣኖቹ “ስልጠናው የድርጅቱን ራዕይ እንዲሳካ ከማድረግ ባልተናነሰ ለግል ሕይወታችን ጠቃሚ ስልጠና በመሆኑ ድርጅቱን እጀግ እናመሰግናለን፡፡” ብለዋል፡፡ “በእርግጥ እኛ ድንቅ ነን ፣ድርጅታችን ድንቅ ነው ፣ሀገራችን ድንቅ ናት”