“በጥራት ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ድርጅት ሆኗል፡፡ ይህ ውጤት እንዴት መጣ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ውጤት ምኞትና ፍላጎት ስላለ ብቻ ሚመጣ አይደለም ፣በልፋትና በድካም እንጂ፡፡ ያለድካም የሚገኝ ውጤት ጊዜያዊና ፈራሽ ነው ፡፡ የሆነ ነገር ሲነካው የሚሟሽሽ ይሆናል፡፡ በድካም በጥረትና በመስዋዕትነት የሚገኝ ውጤት ግን ሁሌም የሚያኮራ ፣በማይገረሰስና በማይናወጥ መሠረት ላይ የፀና ይሆናል፡፡ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የውጤት መሠረትም ቅንጅታዊ ስራ ነው፡፡ ሰራተኛውና አመራሩ በአንድ እጅ ተያይዞ በአንድ ልብ ተቀናጅቶ በአንድ ዓላማ በመሰራቱ ነው ውጤቱ ሊመዘገብ የቻለው ።ሀላፊነትን ተገንዝቦና አውቆ ለሀገርና ለህዝብ ተቆርቋሪ ሆኖ መስራትም ይጠይቃል፡፡ ይህ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ድርጅቱ በርካታ ውጤቶችን ሊያስመዘግብ ችሏል ፡፡ በቀጣይም ለብዙ ተቋማት አርአያ የሆነ ተግባራትን እንደሚያስመዘግብ ባለ ሙሉ እምነት ነኝ፡፡ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆኜ በሰራሁባቸው አመታት በድርጅቱ ውስጥ ያለው የስራ ባህል በጣም የስደስተኛል፡፡ ለሌሎች ተቋማትም ትምህርት የሚሆን ነው፡፡ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሚሰጣቸው የመንግስት ሠራተኞች የድርጅቱ ሰራተኞች እንዴት ህዝብን ማገልገል እንደሚገባና እንደሚቻል ትምህር እየሰጡ ያለበት ሁኔታ በጣም አስደሳች ነው፡፡
Good Job Keep It Up!!!!!