PSTS

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራንስፖርትና የከተማ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢአቶ አሸናፊ ጋዕሚ

የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የጥራት ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል ይገባዋል።መሸለሙ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡ በእርግጥም ይገባዋል፡፡ በመናበብ ክፍተቶችን እያረምን የመጣንበት ጉዳይ ስለነበረ ሁሉንም በቅርብ እንከታተለዋለን፡፡ ለዚህ ተቋም የተሰጠው የጥራት ሽልማት ያንስበት ይሆናል እንጂ አይበዛበትም፡፡ ድርጅቱ የጥራት ሽልማቱን ሲያገኝ የኮሚቴያችን አባላት በሙሉ ነው የተደሰትነው፡፡ የኛም ዓላማ ይኸው ነበር፡፡ ታግሎ ሰርቶ በህዝብ ተመስክሮለት የሚሸለም ድርጅት ነበር ማየት የፈለግነው፡፡ ምኞታችን ተሳክቶ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት እኛንም አሸልሞናል፡፡ የድርጅቱን ሽልማት ክብርና ዝና ለኛም ደርሷል፡፡ በድርጅቱ ኮርተናል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *