የቤቶቹን ቁልፍ ያስረከቡት የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አወል ወግሪስ እንደተናገሩት ” በአንድም በሌላም መልኩ ለሀገር አሰተዋጽኦ የነበራቸውን ሰዎች በመጦሪያ ጊዜአቸው መደገፍ፣ ተገቢ በመሆኑ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤታችን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ይህን ዓይነት በጎ ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።”የቤቶቹን ግንባታ ሙሉ ወጪ በመሸፈን ባመረ መልኩ እንዲጠናቀቅ ያደረገዉ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሲሆን ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ፍሬህይወት ትልቁ እንደተናገሩት በዚህ በጎ ተግባር ላይ በመሳተፍ ተቋሙ እንደተለመደዉ ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣቱ ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸዉ ገልጸዋል። ለመኖር የማይመች ጠባብ ቤቶችን ድርጅቱ 1.2 ሚሊየን ብር ወጭ በማድረግ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ከተሟላ የቤት ዕቃዎች ጋር የሁለት አቅመ ደካማ ጎረቤታሞች ለ86 ዓመት አዛውንት ለአቶ ለማ ደምሴ እና ለወ/ሮ ወርቅነሽ ቱፋ ቤቶችን በአጭር ጊዜ ሰርተን አሰርክበናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ከልተረዳዳን እና ከልተደጋገፍን እንደ ሀገር ድህነትን ማሸነፍ አንችልምና መረዳዳት ባህላችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አሰፈጻሚ የሆኑት አቶ አባወይ ዮሀንስ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው እድሳት ከተደረገላቸው ቤቶች ይህ ቤት እጅግ ደረጃውን ጠብቆ በመሰራቱ ተምሳሌት ሊሆን የሚገባ የቤት እድሳት ነው ብለው እንደነዚህ አቅመ ደካማ አባቶችንና እናቶችን መርዳት ቤተሰብን እንደመርዳት ይቆጠራል ብለው ለቤቶች እድሳት አሰተዋጽኦ ያደረጉትን የትራንስፖርት ሚኒሰቴርንና የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅትን አመሰግነዋል።