የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከ1 እስከ 6 አመት ምንም አይነት የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ላላደረሱ ለ223 የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አበረከተ።በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት ድርጅት ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬ ህይወት ትልቁ ድርጅታቸው በ2013 ዓ.ም 430 ተሽከርካሪዎች በመመደብ በቀን ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑየፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት መቻሉን አብራርተዋል፡፡ አገልግሎት መስጠት ብቻም ሳይሆን አገልግሎቱ ከአደጋ የፀዳ እንዲሆን የተሰጣቸውን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር እየደረሰ ያለውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ለመከላከል የበቁ አሽከርካሪዎችን ማበረታታት በአርዓያነቱ የሚገለፅ ተግባር ነው ብለዋል፡፡ድርጅታቸው ህግ አክባሪ አሽከርካሪዎችን ከማፍራት እና ከማበረታታት ጀምሮ በርካታ ጥረቶችን ማድረግ የተቻለ በመሆኑ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ 8ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ባካሄደው ውድድር የዋንጫ ተሸላሚ መሆን በመቻላቸው ለዚህ ሽልማት ለበቁ 223 የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች ከሰርተፍኬት ጀምሮ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል ብለዋል።እውቅና የተሰጣቸው የድርጅቱ የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች ፥በሰጡን አስተያየት በመልካም የሰራው ውጤት የሠራን ማበረታታት ነገ በሀላፊነት የትራፊክ አደጋን ተከላከሎ የሚያሽከርከር አሽከርካሪን ለመፍጠር ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸውየመንገድ ትራፊክ አደጋ እያደረስ ያለውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ለመቀነስ የበኩላቸውን ሀላፊነት ለመወጣት የበለጠ እንደሚተጉ ተናግረዋል ፡፡