PSTS

ምስጋና

የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ደርጅት ለኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ማህበር በየጊዜው ለሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ ታክመው በዳኑና ወረፋ በመጠበቅ ላይ ባሉ የልብ ሕሙማን ህፃናት ስም ሆኜ ምስጋናዬን ለማቅረብ ነው የመጣሁት” ያለችሁ የማህበሩ አምባሳደር አርቲስት መሠረት መብራቴ “በጎ ከማድረግ የበለጠ በሰማይም በምድርም የሚያኮራ ተግባር የለም፡፡ አሁንም በርካታ የህክምና እርዳታ የሚፈልጉ ህፃናት ወረፋ በመጠበቅ ላይ ናቸው፡፡ እገዛችሁ እንዲቀጥል እንጠይቃለን፡፡” ብላለች፡፡ “የልብ ህሙማን ህፃናቱ ልጆቻችን ናቸው፡፡ እነሱ ታክመው ድነውትልቅ ስራ መስራት የሚችሉ ዜጎቻችን ናቸው፡፡ ልንደግፍ ልንረዳ የህሊናም የሞራልም ግዴታ አለብን፡፡ ድርጅታችንም የልብ ህሙማን ማህበሩን ሲደግፍ ይህን መነሻ አድርጎ ነው፡፡ ”ያሉት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተረ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ አቅም በፈቀደ መጠን በቀጣይም ማህበሩን መደገፋችንን እንቀጥላለን፡፡ ለምስጋና ቢሯችን ድረስ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን፡፡ በርቱ ከጎናችሁ ነን” ብለዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *