በቴክኖሎጂ በሰው ኃይልና በሌሎች ግብአቶች ለመረዳዳትና ለመቀናጀት የሚያስችል የጋራ ስምምነት በፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅትና በአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የመግባቢያ ሰነድ ተፈረሙ፡፡“የዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች መቀመጫ በሆነችው አዲስ አበባ እየተበራከተ የመጣውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ተቀናጅቶ መስራት ግድ ሆኗል፡፡” ያሉት የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ “የብዙሀን ትራንስፖርት በማስፋትና በማቀናጀት መንግስታዊ የሆኑ ተቋማት በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ሰነዱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በዛሬው ዕለት ፊርማ ሰነስርዓቱ ተካሂዷል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “ሁለቱ ድርጅቶች በአዲስ አበባባ እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች የሚሰጡት የትራንስፖርት አገልግሎት በቅንጅትና በትብብር አገልግሎትን ለመስጠት በሰው ኃይል፣ በማቴሪያልና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ይበልጥ አስተማማኝ ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ ከማድረግ በተጨማሪ ድርጅቶቹ ባላቸው ማሽነሪዎች በጋራ በክፍያ አገልግሎት ለመስጠት እንዲሁም የመለዋወጫ እጥረትን ለመፍታትና በትብብር ለመስራት ተስማምተናል” ያሉት ደግሞ የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ትራንስፖርት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገበየሁ ዋቄ ናቸው፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱን የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ እና የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ትራንስፖርት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገበየሁ ዋቄ ተፈራርመዋል፡፡