እንኳን በሰላም ወደ

ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዌብ ሳይት በሰላም መጡ

ውጤታማ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በ አዲስ አበባ በአራቱ ማዕዘናት የሚገኝ አራት የትራንስፖርት አገልግሎት አስተባባሪ ቅርንጫፍ ጽ / ቤት ከፍቷል ፡፡ ምስራቅ ; የምዕራብ ፣ የሰሜን እና የደቡብ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ፡፡

ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት

መንግስት የ ፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛውን የልማት እና የ እድገት ተጠቃሚ ለማድረግ እየወሰዳቸው ካሉት እረምጃዎች ለፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች በ ሰራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓት ከቤት ወደ ሰራ እና ከ ሰራ ወደ ቤት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት አንዱ ሲሆን ይህንንም አገልግሎት ድርጅትን የልማት ድርጅቶችን ለማቋቋም ባወጣው አዋጅ ቁጥር 25/1984 በሚንስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 298/2006 ተቋቁሟል።

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የፐብሊክ ሰራተኛው በከተማው ባለው የትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት ምክኛት ይደርስበት የነበረ ወከባ ፣ እንግልት ፣ እና ወጪ በማስቀረት ምቾቱ እና ድህንነቱ ተጠብቆ በሚፈለገው ጊዜ እና ፍጥነት በአስተማማኝ ሁኔታ ወደ ሰራው እና ወደቤቱ ለማድረስ እንዲችል የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንፖርት አገግሎት አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት መስከረም 5 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በየጊዜው አደረጃጀቱንና የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል ለፐብሊክ ሰርቪሱ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ከ አገልግሎቶቻችን በጥቂቱ

12032672_883784918379009_1251987280345639709_o

የኮንትራት አገልገሎት

ለስብሰባ፣ለኮንፍረንስ ፣ለሀገርህን እወቅ፣ ለስፖርት ክበባትና ለሠራተኞች ዓመታዊ በዓል ታዳሚዎችን ከስፍራ ስፍራ ለማጓጓዝ የድርጅታችን አውቶቡሶች የኮንትራት አገልግሎት እንደሚሰጡ ያውቃሉ?

IMG_5584

ቦሎ

ድርጅታችን በመዲናችን አዲስ አበባ በጥቂት ቦታዎች ብቻ በሚገኘው ዘመናዊ ማሽን በቪዲዮ የታገዘ የተሸከርካሪ የቴክኒክ ምርመራ በተመጣጣኝ ክፍያ በመስጠት ላይ መሆኑን ያውቃሉ?

12291890_906842052739962_8222076209807386064_o

ታክሲ

ከስራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት ውጪ የዘመኑ የቴክኖሎጂ በተገጠመላቸው ምቾታቸው አስተማማኝ በሆኑ አውቶቡሶቻችን የምንሰጠው ህዝብ ትራንስፖርት (ታክሲ) አገልግሎት ተጠቅመው ጊዜንና ገንዘብዎን ቆጥበው ካሰቡበት በፍጥነት ይድረሱ፡፡

ከአውቶቡስ ተጠቃሚዎች የሚጠበቁ ግዴታዎች

  1. ጧት ማታ በሰርቪስ ለመጠቀም የፌደራል ወይም የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኛ
    መሆን ፣
  2. በሰርቪስ ጠዋትና ማታ ለመጠቀም የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት መታወቂያ
    መያዝ
  3. ከአውቶቡስ ጉዞ ሰዓት በፊት 10 ደቂቃ ቀድሞ በመነሻ ቦታ እና ፌርማታ ላይ ተገኝቶ መታወቂያ አሳይቶ መሳፈር
  4. ወደ አውቶቡስ ሲገቡ (ሲሳፈሩ) ከእጅ ቦርሳ ውጭ የአውቶቡሱን ደህንነት እና የሌሎች ተጠቃሚዎች ምቾች
    የሚያውኩ (የቤት እንሰሳት፣ ሻንጣ ፣ ዘንቢል ፣ ጋዝ ፣ዘይት ወዘተ….) ይዞ አለመሳፈር
  5. የአውቶቡሱን ንጽሕና መጠበቅ ሶፍት ፣ ማስቲካ ፣ ወረቀት ወዘተ…….. አለመጣል
  6. በአውቶቡሱ ውስጥ የሚገኙ መጠቀሚያዎች ቴሌቪዥን፣ ወንበር ፣ የደህንነት ቀበቶ ፣ መጋረጃ ፣ ወዘተ …. አለማበላሸት
  7. በከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰዓት ሲጠቀሙ የመስመሩን ሂሳብ ከፍለው ትኬት መያዝ ፣
  8. በጉዞ ላይ እንዳሉ በተቆጣጣሪ ትኬት ወይም መታወቅያ ሲጠየቁ ማሳየት ከጉዞ በኋላ ትኬቱን ቀዶ መጣል
  9. በጉዞ ላይ እያሉ የሌሎች ተጓዦች ምቾትና ደህንነት የሚያውክ ተግባር አለመፈፀም ( ትንኮሳ ፣ ጮክ ብሎ
    ማውራት ፣ በሞባይል ዘፈን ፣ መዝሙር ፣ መንዙማ መክፈት ወዘተ…)
  10. ወደ አውቶቡስ ሲገቡ (ሲሳፈሩ) በሰልፍና በተራ መግባት ፣ በፌርማታ ብቻ መሳፈር እና መውረድ፣
  11. በአውቶቡስ ውስጥ ጫት ፣ ሲጋራ ወይም ሌላ እፅ አለመጠቀም
  12. በከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሳይከፍሉ መጓጓዝ የመስመሩን ታሪፍ አምስት እጥፍ ያስቀጣል፡፡
    በተጨማሪ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ያስጠይቃል፡፡
  13. በአወቶቡስ ውስጥ ደንበኞችንም ሆነ የድርጅቱ ሠራተኞችን መሳደብ ክልክል ነው።
  14. ለአካል ጉዳተኞች ፣ ለነፍሰጡር ሴቶች እና ለአረጋውያን ቅድሚያ መስጠት ግዴታ ነው፡፡
  15. አውቶቡስ ሲሳፈሩ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ያደርጉ
  16.  አውቶቡስ ከተሳፈሩ በኋላ በር እይደገፉ