የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
ከምንሰጣቸው አገልግሎቶች በጥዊቱ
ኮንትራት
ለስብሰባ፣ለኮንፍረንስ ፣ለሀገርህን እወቅ፣ ለስፖርት ክበባትና ለሠራተኞች ዓመታዊ በዓል ታዳሚዎችን ከስፍራ ስፍራ ለማጓጓዝ የድርጅታችን አውቶቡሶች የኮንትራት አገልግሎት እንደሚሰጡ ያውቃሉ? ከሠኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ምቾት ባላቸውና የዘመኑ የቴክኖሎጂ ውጤት በተገጠመላቸው አውቶቡዶቻችን በባስ ካፒቴኖቻችን ስነ ምግባር በመተማመን ነው፡፡
ቦሎ
ድርጅታችን በመዲናችን አዲስ አበባ በጥቂት ቦታዎች ብቻ በሚገኘው ዘመናዊ ማሽን በቪዲዮ የታገዘ የተሸከርካሪ የቴክኒክ ምርመራ በተመጣጣኝ ክፍያ በመስጠት ላይ መሆኑን ያውቃሉ? የቴክኒክ ምርመራውን በብቃት ለተወጡ ተሸከርካሪዎች ብቻ ነው የብቃት ማረጋገጫውን የምንሰጠው አገልግሎታችን ግልፅና በቪዲዎ ቀረፃ የተደገፈ በመሆኑ ስለጥራታችን ሀሳብ አይግባዎ፡፡ ይምጡና ትክክለኛውን የተሸከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ በማድረግ ራስዎንና ወገንዎን ከአደጋ ይጠብቁ፡፡
ታክሲ
ከስራ መግቢያና መውጪያ ሰዓት ውጪ የዘመኑ የቴክኖሎጂ በተገጠመላቸው ምቾታቸው አስተማማኝ በሆኑ አውቶቡሶቻችን የምንሰጠው ህዝብ ትራንስፖርት (ታክሲ) አገልግሎት ተጠቅመው ጊዜንና ገንዘብዎን ቆጥበው ካሰቡበት በፍጥነት ይድረሱ፡፡ በተመጣጣኝ ዋጋ ባስተመማማኝ ፍጥነት በቅን መስተንግዶ ዘና ፈታ ብለው በሁሉም አካባቢዎች በተዘረጋው ታክሲ አውቶቡሶቻችንን ይጠቀሙ፡፡ መገኛችን መሐል ከተማ ከሜክሲኮ አደባባይ ዝቅ ብሎ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ከፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በመሆኑ ሰይደክሙ በቀላሉ ወደ ቢሯችን መጥተው በአጭር ጊዜና በቀልጣፋ መስተንግዶ መኪናዎትን አስጠግነው አሳድሰው ይመለሳሉ፡፡