ዜና እና መረጃዎች

ማርች 8 ተከበረ

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ111 ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ46 ጊዜ የተከበረውን ማርች 8 ከሰራተኞች ጋር አከበረ።”እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል ተከበረውን ቀን በንግግር የከፈቱት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት ትልቁ “ከዚህ በበለጠ ትግል ሴቶች አሁን ካለው የሴት አመራሮች ቁጥር በልጠን መታየት አለብን።ለዚህም በተሰማራንበት የስራ መልክ ውጤታማ መሆን አለብን”ብለዋል።

ማርች 8 ተከበረ Read More »

የክልል መለያን የያዙ ሰሌዳዎችን የሚያስቀር ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሠራጨ ያለዉ መረጃ የተሳሳተ ነዉ፡፡

4ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የመንገድ ትራንስፖርት ረቂቅ አዋጅ ላይ አስፈላጊዉን ግብዓቶችን በማካተት እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መምራቱ ይታወሳል፡፡ሆኖም ግን ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ዉጭ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የክልል መለያ ከተሽከርካሪዎች ሰሌዳ ላይ እንዲነሳ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ መመራቱን የሚገልጽ ዜና እየተዘገበ ስለመሆኑ አረጋግጠናል፡፡በመጀመሪያ መረጃዉ የተሳሳተና ከረቂቅ አዋጁ ይዘት ዉጭ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የክልል መለያን የያዙ ሰሌዳዎችን የሚያስቀር ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ተመራ በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሠራጨ ያለዉ መረጃ የተሳሳተ ነዉ፡፡ Read More »

ጉብኝት ተካሄደ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የመስክ ምልከታና ውይይት አካሄዱ ፡፡የተከበሩ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ በወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የተመራው ኮሚቴ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በሠራተኛ ወደ ስራ መግቢያ ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የጉዞ አቅጣጫዎች በመገኘት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ከመስክ ጉብኝቱ በኋላ ከድርጅቱ ስራ አመራር አባላት ጋር ጥያቄና መልስ

ጉብኝት ተካሄደ Read More »

የተሸከርካሪ ሰሌዳን እናስጨርሳለን በማለት ገንዘብ ከሚጠይቁ ግለሰቦች ህብረተሰቡ መጠበቅ እንዳለበት ተገለፀ

የተሸከርካሪ ሰሌዳን ህትመትና ስርጭት ከትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር በውክልና ተረክቦ ስራውን በማከናወን ላይ ያለው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ጉዳይ እናስፈፅማለን በሚል  ገንዘብ ከሚጠይቁ ግለሰቦች መጠንቀቅ እንዳለበት ገለጸ፡፡ የድርጅቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር  አቶ ሰለሞን አምባቸው በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ የተሸከርካሪ ሰሌዳን በህጋዊ መንገድ ከክልልና ከአስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮዎች ጋር በመተባበር በመስጠት ላይ መሆኑን ገልፀው የተፈጠረው የህትመት ስርጭት አከናዋኝ የባለቤትነትን

የተሸከርካሪ ሰሌዳን እናስጨርሳለን በማለት ገንዘብ ከሚጠይቁ ግለሰቦች ህብረተሰቡ መጠበቅ እንዳለበት ተገለፀ Read More »

ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በመሾምዎ የድርጅታችን ሰራተኛና አመራር የተሰማንን ደስታ እንገልፃለን።የስራ ዘመንዎ እንደ ሁል ጊዜው የተሳካ እንዲሆን እንመኛለን።

ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በመሾምዎ የድርጅታችን ሰራተኛና አመራር የተሰማንን ደስታ እንገልፃለን።የስራ ዘመንዎ እንደ ሁል ጊዜው የተሳካ እንዲሆን እንመኛለን። Read More »

ስልጠና ተሰጠ

የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ስልጠና ለባስ ካፒቴኖች ተሰጠ፡፡ከመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች ለሦስት ተከታታይ ቀናት ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን ከአራቱም አገልግሎት መስጫ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የተወጣጡ ባስ ካፒቴኖች የስልጠናው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ስልጠናው ቀጣይነት እንዳለው የገለፁት የድርጅቱ የመንገድ ትራፊክ ደህንነትና ኢንሹራንስ ቡድን መሪ አቶ ታዬ ታምሩ “ስልጠናው አደጋን ተከላክሎ በማሽከርከር ድርጅቱ እያስመዘገበ ያለውን ውጤት የበለጠ የተሳካ ያደርገዋል፡፡”

ስልጠና ተሰጠ Read More »

“እኛ ድንቅ ነን ድርጅታችን ድንቅ ነው”

የተነቃቃ፣ ለራሱና ለድርጅቱ ራዕይ መሳካት የድርሻውን ለመወጣት የተዘጋጀ ሰራተኛ መፍጠር ውጤቱ እጅግ የጎላ ነው፡፡ይህን ዕውነታ ተገንዝቦና ቆም ብሎ ህልሙን ለማሳካት የሚጥር አመራና ሰራተኛ መኖር አለበት በሚል ቀደም ሲል ለድርጅቱ ስራ አመራር የተሰጠው Motivational Training ወደ ሰራተኛው ወርዶ “እኛ ድንቅ ነን ድርጅታችን ድንቅ ነው”በሚል ርዕስ ከመቶ ለሚበልጡ ሰራተኞች በታወቀው ባለሙያ በዳዊት ድሪምስ ስልጠና ተሰጥቷ።ልለአንድ ቀን ከግማሽ

“እኛ ድንቅ ነን ድርጅታችን ድንቅ ነው” Read More »

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ደስ ብሎናል እንኳን ደስ ያለዎ።ሀገራችንን ወደ ከፍታ የማሻገር ራዕይዎ እንዲሳካ የድርጅታችን ሰራተኛና አመራር ከጎንዎ ነን።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ደስ ብሎናል እንኳን ደስ ያለዎ።ሀገራችንን ወደ ከፍታ የማሻገር ራዕይዎ እንዲሳካ የድርጅታችን ሰራተኛና አመራር ከጎንዎ ነን። Read More »

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሠራተናኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታና የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ አባል

“በጥራት ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ ድርጅት ሆኗል፡፡ ይህ ውጤት እንዴት መጣ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ውጤት ምኞትና ፍላጎት ስላለ ብቻ ሚመጣ አይደለም ፣በልፋትና በድካም እንጂ፡፡ ያለድካም የሚገኝ ውጤት ጊዜያዊና ፈራሽ ነው ፡፡ የሆነ ነገር ሲነካው የሚሟሽሽ ይሆናል፡፡ በድካም በጥረትና በመስዋዕትነት የሚገኝ ውጤት ግን ሁሌም የሚያኮራ ፣በማይገረሰስና በማይናወጥ መሠረት ላይ የፀና ይሆናል፡፡ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሠራተናኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታና የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ አባል Read More »

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራንስፖርትና የከተማ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢአቶ አሸናፊ ጋዕሚ

የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የጥራት ሽልማት ተሸላሚ ሆኗል ይገባዋል።መሸለሙ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም፡፡ በእርግጥም ይገባዋል፡፡ በመናበብ ክፍተቶችን እያረምን የመጣንበት ጉዳይ ስለነበረ ሁሉንም በቅርብ እንከታተለዋለን፡፡ ለዚህ ተቋም የተሰጠው የጥራት ሽልማት ያንስበት ይሆናል እንጂ አይበዛበትም፡፡ ድርጅቱ የጥራት ሽልማቱን ሲያገኝ የኮሚቴያችን አባላት በሙሉ ነው የተደሰትነው፡፡ የኛም ዓላማ ይኸው ነበር፡፡ ታግሎ ሰርቶ በህዝብ ተመስክሮለት የሚሸለም ድርጅት ነበር ማየት

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራንስፖርትና የከተማ ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢአቶ አሸናፊ ጋዕሚ Read More »