Bolgs and news

የአባባ ለማ ቤት ፈርሶ…. ተሰርቶ ተመረቀ፡፡

የቤቶቹን ቁልፍ ያስረከቡት የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አወል ወግሪስ እንደተናገሩት ” በአንድም በሌላም መልኩ ለሀገር አሰተዋጽኦ የነበራቸውን ሰዎች በመጦሪያ ጊዜአቸው መደገፍ፣ ተገቢ በመሆኑ ሚኒስቴር መሰሪያ ቤታችን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር ይህን ዓይነት በጎ ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።”የቤቶቹን ግንባታ ሙሉ ወጪ በመሸፈን ባመረ መልኩ እንዲጠናቀቅ ያደረገዉ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ሲሆን […]

የአባባ ለማ ቤት ፈርሶ…. ተሰርቶ ተመረቀ፡፡ Read More »

ከ1 እስከ 6 አመት የትራፊክ አደጋ ላላደረሱ የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች/ባስ ካፒቴኖቼ/ ልዩ ሽልማት ተበረከተ

የፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከ1 እስከ 6 አመት ምንም አይነት የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ ላላደረሱ ለ223 የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አበረከተ።በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት ድርጅት ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬ ህይወት ትልቁ ድርጅታቸው በ2013 ዓ.ም 430 ተሽከርካሪዎች በመመደብ በቀን ከ100 ሺህ በላይ ለሚሆኑየፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት መቻሉን አብራርተዋል፡፡

ከ1 እስከ 6 አመት የትራፊክ አደጋ ላላደረሱ የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች/ባስ ካፒቴኖቼ/ ልዩ ሽልማት ተበረከተ Read More »

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በአቤት ሆስፒታል በመገኘት የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎችን ጎበኙ፡፡

በትራንስፖርት ሚኒስቴር ዴኤታ በክቡር ኢ/ር የኋላእሸት ጀመረ የሚመራ ቡድን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ከተማ ከአደጋ በኋላ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን የአቤት ሆስፒታል ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም የትራፊክ አደጋ ከደረሰ በኋላ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ አፋጣኝ የህክምና አገልግሎትን ማጠናከር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በአቤት ሆስፒታል በመገኘት የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎችን ጎበኙ፡፡ Read More »

ለፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት

“የህዳሴ ግድብን ከአባይ፣ አባይን ከጣና ለይቶ ማየት ስለማይቻል “በህብር ጣናን እንታደግ” በሚል መሪ ቃል እንቦጭ አረምን ከጣና ሀይቅ ለማስወገድ በተደረገው ሀገር አቀፍ ዘመቻ ላደረጉት አስተዋፅኦ ይህ የምስክር ወረቀት ከምስጋና ጋር ተሰጥቶዎታል፡፡የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጽ/ቤት

ለፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት Read More »

በአንድ ጊዜ አንድ እናት 5 ልጆችን…….

በማወቅ፣ በመሰልጠን፣ ለህሊናና ለትራፊክ ህግ ተገዢ በመሆን ልንከላከለው በምንችለው የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋ በሚያደርሰው ጥፋት ብዙ ጎጆዎች ፈርሰዋል፡፡ ብዙ ቤተሰቦች ተበትነዋል፡፡ አባት እናታቸውን ያጡ ህጻናት ለችግር ተዳርገዋል፡፡ ለእነዚህ ህፃናት አለሁ ብሎ ደራሽ መሆን ፅድቁ በምድርም በሰማይም ነው፡፡ የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በዚሁ አሰቃቂ አደጋ ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን አስተምሮ ለወግ ለማዕረግ ሊያበቃ 5 ህፃናትን

በአንድ ጊዜ አንድ እናት 5 ልጆችን……. Read More »

ምስጋና

የፐብሊክ ሰርቪስ ሠራተኞች ትራንስፖርት አገልግሎት ደርጅት ለኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ማህበር በየጊዜው ለሚያደርገው የገንዘብ ድጋፍ ታክመው በዳኑና ወረፋ በመጠበቅ ላይ ባሉ የልብ ሕሙማን ህፃናት ስም ሆኜ ምስጋናዬን ለማቅረብ ነው የመጣሁት” ያለችሁ የማህበሩ አምባሳደር አርቲስት መሠረት መብራቴ “በጎ ከማድረግ የበለጠ በሰማይም በምድርም የሚያኮራ ተግባር የለም፡፡ አሁንም በርካታ የህክምና እርዳታ የሚፈልጉ ህፃናት ወረፋ በመጠበቅ ላይ ናቸው፡፡ እገዛችሁ እንዲቀጥል

ምስጋና Read More »

ነፍስ ይማር

በባልደረቦቻችን በአቶ ወንድማገኝ አንተነህና በአቶ ሙሉጌታ ብርሀኑ ህልፈት የተሰማኝን ከባድ ሀዘን በራሴ እና በድርጅታችን ስም እገልፃለሁ።ለቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው ፈጣሪ መፅናናትን ይስጥልን። ወ/ሮ ፍሬህይወት ትልቁ ዋና ዳይሬክተር

ነፍስ ይማር Read More »