Bolgs and news

“በጎነት ለሀገር ብልፅግና”

“በጎነት ለራስ ነው። በጎነት ለተቋም ነው ።በጎነት ለሀገር ነው፡፡ ሰው በጎ ሲሆን ያለውን ይከፍላል፣ ሰው በጎ ሲሆን ያጣውን ይጎበኛል፣ ሰው በጎ ሲሆን የሌለውን ይረዳል፣ የተከፋውን ያፅናናል፣ የታመመውን ይጠይቃል። ዜጋ በጎ ሲሆን ሀገር በጎ ትሆናለች፣ ብልፅግና ከበጎ ጋር አብሮ አለ ።ሁሉም በጎ ከሆነ ሀገር ከብለፅግና ማማ ላይ ከፍ ትላለች ።ዛሬ ለዚህ ነው ድርጅታችን ካለው ውስን በጀት […]

“በጎነት ለሀገር ብልፅግና” Read More »

ሴት ሰራተኞች

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወነውን የአረንጓዴ ልማት ለመደገፍ ከአገልግሎ ሰራተኞች ጋር ከተከሉት ችግኝ ባሻገር የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሴት ሠራተኞች ብቻ ተሳታፊ የሆኑበት የችግኝ ተከላ ተከናወነ፡፡ በአንድነት ፓርክ በተከናወነውን የችግኝ ተከላ ከአንድ ሺህ በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉን የገለፁት የድርጅቱ የስርዓተ ፆታና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ተወካይ ወ/ሮ ወይንሸት ኪዳነማርያም “መትከል ብቻ ሳይሆን የተከልነውን ተንከባክበን ለማሳደግ ቃል

ሴት ሰራተኞች Read More »

መሴ ኦያያ!

ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ፣ የብስራት FM መስራችና ባለቤት ጋዜጠኛ መሰለ መንግስቱ (መሴ) ወደ ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ጎራ ብሎ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝቷል፡፡ በተለይ በቅርቡ ልዩ ሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ለመስጠት ተመርተው ዝግጁ የሆኑ አውቶቡሶችን የጎበኘው ጋዜጠኛ መሰለ መንግስቱ በሰለጠኑት ሀገራት ያያቸውን ማቀዝቀዣ፣ መፀዳጃ፣ቻርጀርና ዋይፋይ እንዲሁም አርቴፊሻል ኢንተለጀንት የተገጠመላቸውን አውቶቡሶች መጎብኘት በመቻሉ እጅግ እንደተደሰተና ኩራት እንደተሰማው ገልጿል፡፡

መሴ ኦያያ! Read More »

የሚኒስትሮቹ ጉብኝት

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ፡፡ በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍሬሕይወት ትልቁ ማብራሪያ የተጀመረው የሚኒስቴሮቹ ጉብኝት በተለይ በቅርቡ ተመርተው አገልግሎት መስጠት የሚጀምሩትን ልዩ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች ጎብኝተዋል፡፡ “ልዩ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶቹ በተለይ አደጋን ተከላክሎ ለማሽከርከር የሚያስችሉ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው ፣አሽከርካሪው ለአደጋ የሚያጋልጡ ተግባራት ሲፈፀሙ ቀጥታ ለተቆጣጣሪው አካል ሪፖርት የሚያደርጉ

የሚኒስትሮቹ ጉብኝት Read More »

#Ethiopia! Great stuff launching electric car adoption for a sustainable development!

የኢትዮጵያ የትራንስፖትት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቂያ መድረክ እና 60 ተሽከርካሪዎችን በ40 የቻርጂንግ ማእከላት በመታገዝ ለ1ወር ያዘጋጀዉን የነፃ ትራንስፖርት አገልግሎት አስጀምሯል፡፡ ተቋሙ እያደገ የመጣዉን የነዳጅ ተጠቃሚነት አማራጭ የሀይል ምንጭ በሚጠቀሙ እና ለአካባቢ ተስማሚ በሆኑ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ለመተካት እየሰራም ይገኛል፡፡ በዚህም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አገራችን ያላትን ሰፊ የታዳሽ ሀይል አቅም እያደገ

#Ethiopia! Great stuff launching electric car adoption for a sustainable development! Read More »

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዘመናዊ ሃገር አቋራጭ አውቶብሶች ተረከበ

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዳስትሪ ያመረታቸውን ዘመናዊ ሃገር አቋራጭ አውቶብሶችን በዛሬው እለት ለፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት አስረከበ። በእለቱም የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አብርሀም በላይ እንደተናገሩት የምርቶችን ጥራት በማሳደግ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነታችንን ማሳደግ አለብን ብለዋል። የትራንስፖርት እና የሎጅስቲክስ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደገለፁት፤ በቀጣይ ከግሩፑ ጋር

የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ዘመናዊ ሃገር አቋራጭ አውቶብሶች ተረከበ Read More »

ውይይት ተካሄደ

ከቢሾፍቱ፣ ከሰንዳፋ፣ከጫንጮ፣ ከሆታ፣ ከሱሉልታና ከሌሎች ከአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ተተቃሚዎች የአውቶቡስ አስተባባሪዎች ተወካዮች ከፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት የማኔጅመንት አባላት ጋር በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ ውይት አካሄዱ፡፡ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የአገልግሎት ዋና ዳይክተር ወ/ሮ ፍሬህይወት ትልቁ “አዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች የትራንስፖርት ተጠቃሚ ተወካዮች ዘወትር አገልግሎት አሰጣጣችን የተሳካ

ውይይት ተካሄደ Read More »

“የሰው ወርቅ አያደምቅ”

ጠዋት በማለዳ ባስ ካፒቴን ሳሙኤል ተስፋዬ የጎን ቁጥር 5071 እያሽከረከሩ በርካታ የፐብሊክ ሰርቪስ ተሳፋሪዎችን አሳፍረው ከሱሉልታ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ነበሩ፡፡ በእለቱ መምህር ታደሰ ጌታቸው ወደ ሚያስተምሩበት ፀሐይ ጮራ ትምህርት ቤት የሚያስተምሩትን ትምህርት በመንገድ ላይ እየከለሱ ተጉዘው ትምህርት ቤታቸው ደረሱና ወረዱ፡፡ ግን ሞባይላቸውን ከኪሳቸው ሲፈልጉት የለም፡፡ “ከመደንገጤ የተነሳ የት እንደጣልኩት ለመገመት እንኳን ተቸግሬ ነበር፡፡

“የሰው ወርቅ አያደምቅ” Read More »